05/06/2026
በጥንቃቄ መንዳት፣ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት!
አሁን በመገናኛ አካባቢ የተከሰተውን የትራፊክ አደጋ ስንመለከት፣ ሁላችንም ለራሳችን እና ለሌሎች ወገኖቻችን ደህንነት የበለጠ ትኩረት መስጠት እንዳለብን ያስታውሰናል።
የምንወዳቸውን ቤተሰቦች እና ወገኖቻችንን ሰላም መጠበቅ የሚጀምረው ከመንገድ ላይ ባለን ጥንቃቄ ነው። እባካችሁ ፍጥነትን በመቀነስ፣ የትራፊክ ህግጋትን በማክበር እና በትዕግስት በመንዳት የራሳችንን እና የሌሎችን ህይወት እንታደግ።
የጉዞ ፍጻሜያችን ሁሌም ደስታ ነው። ሁሉም አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ወደ ቤታችሁ በሰላም እንድትገቡ መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን። አደጋን በመከላከል የሰው ህይወትን እንታደግ።