Lumax property management plc.

Website

Lumax property management plc. Welcome to LuMax property management PLC.

LuMax is comprised of highly dedicated teams of real estate professionals and Lawyes working together diligently to raise standard of excellence of property industry In Addis Ababa.

👉ንብረትዎን ማስተዳደር አስቸጋሪ ሆኖብዎታል? 👉ታማኝ ሰው አተዋል? 👉በርቀት አልያም በተለያየ ምክኒያት ከተከራይ ጋር ያሎትን ጉዳዮች መከታተል አልቻሉም? 👉ቤት መሸጥ ወይም መግዛት ፈልገው ...
28/08/2026

👉ንብረትዎን ማስተዳደር አስቸጋሪ ሆኖብዎታል?
👉ታማኝ ሰው አተዋል?
👉በርቀት አልያም በተለያየ ምክኒያት ከተከራይ ጋር ያሎትን ጉዳዮች መከታተል አልቻሉም?
👉ቤት መሸጥ ወይም መግዛት ፈልገው የህግ ባለሞያ ምክር ይሻሉ?
💼በህግ ባለሞያ የታገዘ ታማኝ ህጋዊ የንብረት አስተዳዳሪ ድርጅት ይፈልጋሉ?

እርስዎ የንብረቱ ባለቤት ይሁኑ፤ እኛ የማስተዳደር ኃላፊነቱን እንወስዳለን።

LUMAX PROPERTY MANAGEMENT
1. የመኖርያ ቤት: የንግድ ቤቶችንና ህንጻዎችን እናስተዳድራለን።
2. የቤት ሻጭ እና ገዢን እናገናኛለን።
3. በንብረት አስተዳደር: በቤት ሽያጭ እና ግዢ ዙርያ የህግ ምክር አገልግሎት እንሰጣለን።

ከሌሎች ንብረት አስተዳዳሪዎች LUMAX PROPERTY MANAGEMENT የሚለየው:-
1. በህግ ባለሞያ እና በሪልስቴት ባለሞያ የተደራጀ በመሆኑ የሚፈልጉትን አገልግሎት በታማኝነት እናቀርባለን።
2. እኛ ኪራይ ብቻ አንሰበስብም፤ ንብረትዎን እንጠብቃለን።
3. የኪራይ ውል፣ የተከራይ ጉዳዮች እና ሌሎች የሕግ ጉዳዮችን በባለሙያ እንከታተላለን።
4. አለመግባባቶች እና የተከራይ ችግሮች ከተፈጠሩ በኋላ ብቻ ሳይሆን፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ ለመከላከል እንሰራለን።

LUMAX PROPERTY MANAGEMENT ንብረት ብቻ አናስተዳድርም፤ የባለቤቱን መብት፣ ገቢ እና ንብረቱንም እንጠብቃለን እናስጠብቃለን።
ቤት ብቻ አናሻሽጥም ቤት ከመግዛቶ በፊትም ማድረግ ያለቦትን ጥንቃቄ እንመክራለን ከገዙ በኃላ የባለቤት መብቶ ላይ ዋስትና እንዲኖሮት እናግዛለን ::

ድረ-ገጽ: https://lumaxpromang.com/properties
የፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/profile.php?id=61590577374329
ቴሌግራም: https://t.me/+7Lq9tG8mGqUwY2E0
ስልክ ቁጥር : 091 100 2861

#የንብረትአስተዳደር #የቤትሽያጭ #የህግምክር #ሪልእስቴት

06/08/2026

LUMAX Property Management Plc.

የመኖርያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ 1320/2016 ዓላማ፣ በተግባር እየታየ ያለው ችግር እና መፍትሄዎቹ፦

የአዋጁ ዋና ዓላማ የመኖርያ ቤት ኪራይ ዋጋ ከጊዜ ወደ ግዜ እየናረ በመምጣቱ የማህበረሰቡን አቅም ያገናዘበ ተመጣጣኝ እንዲሆን ለማድረግ በማሰብ ሲሆን እንዲሁም የመኖርያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር ግልጽነት እና ተጠያቂነት እንዲኖረው ለማድረግ ታስቦ የወጣ ነው፡፡ ሆኖም አዋጁን ከማስፈጸም አኳያ በርካታ ችግሮች ይታያሉ፦

የአዋጁ ዋና አላማ የኪራይ ዋጋ መናርን መቆጣጠር ቢሆንም በተግባር መሬት ላይ እየታየ ያለው ችግር ከአዋጁ አላማ ተቃራኒ የሆነ እና የመኖርያ ቤት የኪራይ ዋጋ ከእጥፍ በላይ እየጨመረ መምጣቱ ነው፡፡ ለዚህም ዋነኛ ምክኒያት አከራዮች በፊት የተከራየም ሆነ አዲስ ቤት ሲያከራዩ ዋጋ ለሁለት አመት መጨመር አንችልም በማለት የኪራይ ዋጋውን በከፍተኛ ሁኔታ ሰቅሎ በማከራየት ነው፣

አከራይ የሁለት አመት ውሉ ካለቀ በኋላ ዋጋ ጨምሮ ለማከራየት ሲል፣ “እራሴ ልኖርበት ነው፣ ከአሁን በኋላ አላከራየውም፣ ዘመድ ሊኖርበት ነው...” እና የተለያየ ምክኒያት በመደርደር ተከራይን አስወጥቶ ዋጋ ጨምሮ ለሌላ ሰው የማከራየት ችግር ይስተዋላል፡፡ ለሌላ ሰው ባያከራዩ እንኳን ያለውን ተከራይ ዋጋ እንዲጨምር በማድረግ ነገር ግን የኪራይ ክፍያውን በሌላ መንገድ በመቀባበል ህጉን ሲጥሡ ይታያል፣

በአከራይ እና ተከራይ የተለያዩ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ የተፈጠረውን አለመግባባት ከህግ አግባብ ለመፍታት ወደ ተቆጣጣሪ አካላት ሲሄዱ፣ አንዳንድ የወረዳ ባለሞያዎች መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ የግል ጥቅምን የማስቀደም ሁኔታ ይስተዋላል፣

ከላይ በተጠቀሱት ምክኒያቶች የቤት ኪራይ በመናሩ ተከራዮች እና ቤተሰቦቻቸው ተረጋግተው አንድ ቦታ መኖር እንዳይችሉ እና የበርካታ ቤተሰቦችን ኑሮ እያከበደው መጥቷል፡፡

የመፍትሄ ሃሳቦች ፦

ተመሳሳይ መኖርያ ቤቶች ላይ ሰፊ የዋጋ ልዩነት እንዳይኖር አዲስ የሚከራዩትም ሆነ ቀድሞ በወረዳ ተመዝግበው እየተከራዩ ያሉ መኖርያ ቤቶች አከራይንም ሆነ ተከራይን በማይጎዳ መልኩ ስታንዳርድ የሆነ የኪራይ የገበያ ዋጋ ማስቀመጥ ቢቻል፣

በተቆጣጣሪ አካሉ በየአመቱ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ ተከራይንም ሆነ አከራይን በማይጎዳ እና የኑሮ ግሽበቱን ባገናዘበ መልኩ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ቢደረግ፣

ወረዳዎች የአከራይ ተከራይ መረጃዎችን በዘመናዊ እና በተደራጀ ሁኔታ ማስቀመጥ ቢችሉ፡፡ ተዋዋዮች ለኪራይ እድሳት ሲመጡ ቤቱ አዲስ ወይም ቀድሞ የተከራየ መሆኑን በቀላሉ መለየት ከተቻለ እና ቀድሞ የተከራየበት ዋጋን መለየት ከተቻለ፣ አከራይ ከዚህ ቀደም ባከራየው ቤት ላይ እንደፈለገው የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርግ ይረዳል፣

አዋጁን በሚጥሱ አከራይም ሆነ ተከራይ ላይ ጥቆማ ሲቀርብ ፣ ተቆጣጣሪ አካላት ጉዳዩን በገለልተኝነት መርምረው እና አጣርተው በአዋጁ የተጠቀሱትን ቅጣቶች ተግባራዊ ማድረግ ቢቻል፣

ተቆጣጣሪ አካላት አዋጁን በአግባቡ እንዲያስፈጽሙ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት እንዲሁም ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ፣ የስነምግባር ችግር ባለባቸው ባለሞያዎች ላይ እርምጃ መውሰድ፡፡

አዋጁን ጥሰው በሚገኙ አካላት ጥቆማ በሚቀርብበት ግዜ ቅሬታውን ተቀብለው የሚያዩ ተቋማት እና የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አደረጃጀትን ማጠናከር፡፡

LUMAX Property Management Plc

LUMAX Pro.Mang.plcየአከራይ ተከራይ የውል ዘመን  ካለቀ በኋላ ተከራይ የኪራይ ውሉ እንዲታደስለት አከራይን ማስገደድ ይችላል?በመኖርያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ 132...
31/07/2026

LUMAX Pro.Mang.plc
የአከራይ ተከራይ የውል ዘመን ካለቀ በኋላ ተከራይ የኪራይ ውሉ እንዲታደስለት አከራይን ማስገደድ ይችላል?
በመኖርያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ 1320/2016 መሰረት የመኖርያ ቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት አመት ማነስ እንደሌለበት ያዛል፡፡ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ እንደሚታየው አከራይ “የኪራይ ውላችን አልቋል ውል አላድስም” በሚልበት ወቅት ተከራይ ደግሞ “የማስወጣት መብት የለህም ውሉን የማደስ ግዴታ አለብክ” በማለት ቤቱን ለመልቀቅ ፍቃደኝ ያለመሆን ነገር ይስተዋላል፡፡ አብዛኛው የመኖርያ ቤት ኪራይ እንዲቆጣጠሩ ስልጣን የተሰጣቸው የወረዳ እና ክ/ከተማ ባለሞያዎችም ውሉ ቢያልቅም እንኳን አከራይ ውሉን አድሶ ሊቀጥል ይገባል እንጂ ውሉን የማቋረጥ ስልጣን የለውም የሚል አቋም የያዙ ይመስላል፡፡
የውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት እንደማይቻል አዋጁ ይደነግጋል፡፡ ሆኖም የኪራይ ውል ዘመኑ ካበቃ አከራይ ውሉን ለማደስ አይገደድም፡፡ አከራይ እና ተከራይ ውሉን ለማደስ በጽሁፍ እስካልተስማሙ ድረስ ውሉ ሊቀጥል ወይም ሊታደስ አይችልም (አንቀጽ 11(1) እና 6(7)) ፡፡
በመሆኑም የኪራይ የውል ዘመን ከተጠናቀቀ ተከራይ ውሉ እንዲታደስለት አከራይን ማስገደድ አይችልም ነገር ግን አከራይ እና ተከራይ ከተስማሙ ውሉን ሊያራዝሙት እና የአከራይ ተከራይ ውል ሊያድሱ ይችላሉ፡፡

16/07/2026

Property Management

Our company also keeps our client property safe and make the property habitable. Our property management service includes; -

Advertising the property and carefully examining tenants, inspecti ng the property before the tenant moved in moved out of the property

Renting, collecting rent, securing security deposit

Handling legal cases if any raised

Setting budget for the property management, keeping details of financial records, assisting owners during tax payment process, keeping records of rental collection on time

Drafting contracts, laws and rules

Repairing, maintenances, updating facility, landscaping, gardening, cleaning, security etc.

LUMAX pro.mang.plc.

16/07/2026

Welcome to LuMax, your trusted partner in property management and legal solutions. At LuMax, we specialize in providing accessible and expert-driven solutions for property owners and tenants alike. Our dedicated team comprises astute lawyers and seasoned property professionals with extensive experience in managing, selling, buying, and renting properties across national and international landscapes.

LuMax is comprised of highly dedicated teams of real estate professionals and lawyers working together diligently to raise standards of excellence of the property industry in Addis Ababa. We work with investors, landlords, and tenants, making buying, selling, renting and managing property easier and stress free.

We assist families and individuals to realize their dreams through reliable services, partnering with you for a smoother, more rewarding journey in property management and investment.

LUMAX PRO. MANG. PLC
LINK 👇👇👇

14/07/2026

በሕግ ባለሞያ የተደገፈ ፕሮፌሽናል የንብረት አስተዳዳሪ የሚሰጠው አገልግሎት፦
✔ ጠንካራ ህጋዊ መሰረት ያለው የኪራይ ውል በማዘጋጀት ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ክርክሮችን ይቀንሳል።
✔ የባለንብረቱን እና የተከራዩን መብትና ግዴታ በግልጽ ያስቀምጣል።
✔ የኪራይ ክፍያ መዘግየት፣ የውል መጣስ ወይም ሌሎች ክርክሮች ሲከሰቱ በሕግ አግባብ መፍትሔ እንዲገኝ ያግዛል።
✔ ሰነዶችንና መረጃዎችን በአግባቡ ይይዛል።
✔ ሊፈጠሩ የሚችሉ የገንዘብ ኪሳራዎችንና የፍርድ ቤት ክርክሮችን ይቀንሳል።
በህግ ባለሞያ የታገዘ የንብረት አስተዳደር ኪራይ መሰብሰብ ብቻ ሳይሆን የባለንብረቱን መብት፣ ንብረቱን እና ኢንቨስትመንቱን በሕግ ይጠብቃል::
LUMAX Property Management

LU/MAX Pro. Mang. plcይህ ማስታወቅያ 1ኛ ግለሰቦች በውልና ማስረጃ ቤት ገዝተው የስም ዝውውር ያላደረጉ እንዲያደርጉ የሚያሳስብ ሲሆን 2ኛ የሊዝ ክፍያ ያልፈጸሙ አልሚዎች ክፍያ እ...
09/07/2026

LU/MAX Pro. Mang. plc

ይህ ማስታወቅያ 1ኛ ግለሰቦች በውልና ማስረጃ ቤት ገዝተው የስም ዝውውር ያላደረጉ እንዲያደርጉ የሚያሳስብ ሲሆን 2ኛ የሊዝ ክፍያ ያልፈጸሙ አልሚዎች ክፍያ እንዲፈጽሙ ካልከፈሉ በአዋጁ መሰረት እርምጃ እንደሚወሰድባቸው የሚገልጽ ነው፡፡

የገዙትን ቤት አለማስመዝገብ እና የስም ዝውውር አለማድረግ በርካታ አደጋዎች ያሉት ሲሆን በዋናነት በህጋዊ መንገድ መሸጥ መለወጥ አለመቻል፣ ንብረቱን አስይዞ ብድር ለመበርደር ወይም ዋስትና ለማስያዝ አለመቻል፣ በተለይም ለንብረቶ አደጋ የሚሆነው የገዛሁት ቤት ንብረቴ ነው ብለው ስም ሳያዞሩ እና ሽያጩን ሳያስመዘግቡ ተዝናንተው ቁጭ ባሉበት ሻጭ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ያንኑ የገዙትን ንብረት ቢሸጠው፣ የገዙትን ንብረት አስይዞ ብድር ቢበደርበት ወይም ለዋስትና ቢያሲዘው ህጉ በቅን ልቦና ለገዛው ሶስተኛ ወገን ጥበቃ ስለሚያደርግ ንብረትን እስከማጣት ለሚደርስ አደጋ ያጋልጣል፡፡

ምንም እንኳን የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ የማውጣት ተግባር በጊዜ ገደብ ያልተገደበ ቢሆንም የአስተዳደሩ አስመዝግቡ ማሳሰቢያ ከጉዳቱ ጥቅሙ ስለሚያመዝን ማስመዝገቡ ይመረጣል፡፡

የሊዝ ክፍያን አስመልክቶ የሊዝ የመክፈያ ጊዜ ቢያልፍ ምንድነው ቅጣቱ ለሚለው ፦ በሊዝ አዋጅ 721/2004 አንቀጽ20 እና 21 መሰረት በየአመቱ ወቅቱን ጠብቆ ያለበትን የሊዝ ክፍያ የማይከፍል ግለሰብ በዘገዩ የብድር ከፋዮች ላይ ንግድ ባንክ በሚጥለው የቅጣት ተመን መሰረት የሊዝ ክፍያውን ተቀጥተው ይከፍላሉ ይላል፡፡ ነገር ግን የሊዝ ባለይዞታው የሶስት አመት ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካልከፈለ የሚመለከተው አካል ንብረቱን ይዞ በመሸጥ ለውዝፍ እዳው መክፈያ ሊያውለው ይችላል፡፡

በአስተዳደሩ የተለጠፈው የሊዝ ክፍያ ክፈሉ የሚለው ማስታወቅያ ለአልሚዎች የተነገረ ቢሆንም ለማንኛውም አላማ በሊዝ ቦታ የተረከበ ግለሰብ በዚህ አዋጅ ስለሚገደድ የሊዝ ክፍያውን በወቅቱ መክፈል ከሚመጣ አላስፈላጊ ወጪ እና ኪሳራ ይጠበቃል፡፡

ጠበቃ እና የህግ አማካሪ ፍሬህይወት ወዬሶ

Address

Semit Safari
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lumax property management plc. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category