01/06/2024
ሪል ስቴት ሊክዊዲቲ ሪስክ።
ሪል ስቴትን በዋጋው ለመሸጥ አለመቻል ችግር።
Real estate Liquidity Risk in Ethiopia.
| ሊክዊዲቲ ሪስክ ማለት አንድ ንብረት የገበያን ዋጋ ሳያናጋ መሸጥ መለወጥ ያለመቻል ችግር ማለት ነው።
የሪል እስቴት ዘርፍ በዘርፉ ውስጥ ከሚጠበቁት ፈተናዎች ውስጥ አንዱ የሆነው በዋጋው ለመሸጥ አለመቻል ችግር (liquidity risk) ከገጠመው ሰንበትበት ቢልም አልሚዎች አሁንም ለችግሩ ማፍትሄ የሚሆን ነገር ይዘው ብቅ ሲሉ አይታዩም። ነገርየው መፍትሄ ካልተሰጠው እየባሰና እየተባባሰ እንደሚሄድ ሊገባቸው ይገባል።
የሪል እስቴቱ ዘርፍ Liquidity risk ውስጥ እንደገባ የሚያስረዱ ናቸው ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል አብዛኛውን ካሟላ አመት ሊደፍን ነው።
ለምሳሌ:-
፩) በየጊዜው መለኪያ (በወር/በ፫ወር...) የሚሸጡ ቤቶች ቁጥር ማነስ
፪) አንድን ቤት ለመሸጥ የሚወስደው ጊዜ መርዘም
፫) የጠያቂ/ጎብኚ መቀነስ
፬) ለመገንቢያ የሚውል ገንዘብ ለማግኘት መቸገር
፭) የዋጋ መቀነስ ( አንድ ቤት ለሚገዛ በግማሽ ዋጋ...)
፮) ለገበያ ወጥተው ገዢ የማያገኙ ቤቶች ቁጥር መበራከት
ከላይ የተጠቃቀሱትን ዘርፉ ካሟላ ቢቆይም በብዛት በአልሚዎች የተሰጠው መፍትሄ የብራንድ አምባሳደር የሚሆኑ ታዋቂ ግለሰቦችን መቅጠርና/ ወይም ማስታወቂያ ማንጋጋት እንጂ ሁነኛ የሚባል መፍትሄ አይደለም።
በዚህ አይነት ወቅት የሚመከሩ እርምጃዎች ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል የሚከተሉትን መጠቃቀስ ይቻላል:-
፩) ያልተነኩ የሪል እስቴት ዘርፎችን መርጦ ኢንቨስት ማድረግ
፪) ከተመሳሳይ ታሳቢ ደንበኛ ( Target group) ወጥቶ ያልተነካውን ተደራሽ ማድረግ
፫) ሌሎች ካሽ ያላቸውን ወገኖች በመጋበዝ ጥቅምን አጋርቶ አብሮ መስራት
፬) ከቀጥታ ሽያጭ ባሻገር የተለያዩ ገንዘብ ሊገኝባቸው የሚችሉ መንገዶችን መቀየስና መተግበር
፭) ገበያውንና የሃገር ኢኮኖሚን በንቃት መከታተልና መገምገም። በመረጃና በባለሙያ በሚሰጥ የመረጃ ትንተና ኢንቨስት ማድረግ ናቸው።
በ ደሳለኝ ከበደ
(አቶ ደሳለኝ ከበደ ሲቪል መሀንዲስ፣ ገንቢ፣ አሰልጣኝ እና ጸሀፊ ሲሆኑ በግንባታው ዘርፍ ላይ ሰፊ ተሞክሮ ያላቸው ባለሙያ ናቸው)
ethiopian architecture and urbanism