Ethio71

Ethio71 Ethiopian

14/03/2025

MERID - MERIDP smart ethiopian oldis rimx/Ethiopian oldis best oldscool flash buck times forever

የሴኔጋል ፕሬዝደንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ አዲስ አበባ ገቡአዲስ አበባ፤ የካቲት 06/2017(ኢዜአ)፦ የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ለ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ አዲስ አ...
13/02/2025

የሴኔጋል ፕሬዝደንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 06/2017(ኢዜአ)፦ የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ለ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ አዲስ አበባ ገብተዋል።
በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ መሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛል።
በዚህም የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ለሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የፍትህ ሚኒስትር ሀና አርዓያስላሴ አቀባበል አደርገውላቸዋል።
38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ "የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን" በሚል መሪ ሀሳብ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ሱዳን ሩሲያ በቀይ ባሕር ላይ የጦር ሰፈር መመሥረት የሚያስችላትን የመጨረሻውን ስምምነት ከሩሲያ ጋር መፈራረሟን አሳወቀች።ስምምነቱ መጀመሪያ ላይ የተደረገው ከሥልጣን ከተወገዱት ፕሬዝዳንት ኦ...
13/02/2025

ሱዳን ሩሲያ በቀይ ባሕር ላይ የጦር ሰፈር መመሥረት የሚያስችላትን የመጨረሻውን ስምምነት ከሩሲያ ጋር መፈራረሟን አሳወቀች።
ስምምነቱ መጀመሪያ ላይ የተደረገው ከሥልጣን ከተወገዱት ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አል በሺር ጋር ሲሆን፣ በኋላ ላይ የአገሪቱን መንበር የተቆጣጠረው ወታደራዊ መንግሥት ጉዳዩን እየተመለከተው መሆን ተናግሮ ነበር።

በምያንማር በሚገኙ የሳይበር ወንጀል ካምፖች በግዳጅ ሰራተኝነት ተይዘው የነበሩ "138 ኢትዮጵያውያን" ተለቅቀው በትናንትናው ዕለት ወደ ታይላንድ መግባታቸውን በሀገሪቱ የሚገኝ መንግሥታዊ ያል...
13/02/2025

በምያንማር በሚገኙ የሳይበር ወንጀል ካምፖች በግዳጅ ሰራተኝነት ተይዘው የነበሩ "138 ኢትዮጵያውያን" ተለቅቀው በትናንትናው ዕለት ወደ ታይላንድ መግባታቸውን በሀገሪቱ የሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ምንጮች ለቢቢሲ አማርኛ ተናገሩ።

11/02/2025

Address

Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio71 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category