የጋሞ እና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ሰብከት በደራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት መነና ቅ/ሚ/ቤ/ክ/ማ ገጽ

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Minch'
  • የጋሞ እና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ሰብከት በደራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት መነና ቅ/ሚ/ቤ/ክ/ማ ገጽ

የጋሞ እና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ሰብከት በደራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት መነና ቅ/ሚ/ቤ/ክ/ማ ገጽ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የጋሞ እና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ሰብከት በደራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት መነና ቅ/ሚ/ቤ/ክ/ማ ገጽ, Real Estate, Arbaminch, Arba Minch'.

‎   ።።። የንግስ በዓል ጥሪ‎የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል›› (መዝ. 33፤7)‎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን .‎እንኳን ለገናናው መላአክ...
16/11/2025

‎ ።።። የንግስ በዓል ጥሪ
‎የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል›› (መዝ. 33፤7)
‎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን .
‎እንኳን ለገናናው መላአክ ቅዱስ ሚካኤል አሜታው ክብር በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ እያለን
‎በጋሞ እና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት በደራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት ጥንታዊ ከ189 በላይ የቆየው መነና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ህዳር 12/2018 ዓ/ም የታላቁ መላእክት አለቃ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ስለሚከበር በዕለቱ በዓሉ ላይ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
‎
‎መነና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ጽ/ቤት።
‎
‎
‎

‎   ።።። የንግስ በዓል ጥሪ‎የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል›› (መዝ. 33፤7)‎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን .‎እንኳን ለገናናው መላአክ...
16/11/2025

‎ ።።። የንግስ በዓል ጥሪ
‎የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል›› (መዝ. 33፤7)
‎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን .
‎እንኳን ለገናናው መላአክ ቅዱስ ሚካኤል አሜታው ክብር በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ እያለን
‎በጋሞ እና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት በደራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት ጥንታዊ ከ189 በላይ የቆየው መነና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ህዳር 12/2018 ዓ/ም የታላቁ መላእክት አለቃ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ስለሚከበር በዕለቱ በዓሉ ላይ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
‎
‎መነና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ጽ/ቤት።
‎
‎
‎

“ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን።” ሮሜ ፰፥፴፮በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ ፲፬ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተሰምቷል።ከቅርብ ጊዜ ...
29/10/2025

“ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን።” ሮሜ ፰፥፴፮

በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ ፲፬ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተሰምቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዝተን እየተለማመድነው የመጣነው የኦርቶዶክሳውያን ሞት ሊበቃ እና የሰው ልጆች ሁሉ የመኖር ሰብዓዊ መብት ሊረጋገጥ ይገባል።

በአካባቢው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በተደጋጋሚ በአማኙ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት ሊያስቆሙ እና መፍትሔ ሊያበጁለት ይገባል።

ለወደፊቱም ቢሆን እንደ ቤተ ክርስቲያን የሚጠበቁብንን በርካታ ሥራዎች አለመሥራታችን ትውልዱን ዋጋ እያስከፈለው እንዳይኖር ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ መሥራት የሚገባን አያሌ ተግባራት መኖራቸውን መዘንጋት የለብንም።

በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን ዕረፍተ ነፍስን ያድልልን፤ ለቤተሰቦቻቸው አጽናኝ ቅዱስ መንፈስን ይላክላቸው።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !

አባ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ

የጋሞ አብያተክርስትያናት የጋራ ልማት እና በጋሞኛ ቋንቋ ስብከተ ወንጌል አስተባባሪ ኮሚቴ የጋሞ እናቶች እና ወጣቶች የመስቀል በዓል ዝማሬ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ገለጹ።===========...
22/09/2025

የጋሞ አብያተክርስትያናት የጋራ ልማት እና በጋሞኛ ቋንቋ ስብከተ ወንጌል አስተባባሪ ኮሚቴ የጋሞ እናቶች እና ወጣቶች የመስቀል በዓል ዝማሬ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ገለጹ።
=====================

መስከረም ፲፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ/ም የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት ሚዲያ- አርባ ምንጭ

ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ በዘመኑ ፍጻሜ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ፣ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ፣ ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት ተሰቅሎ በመሞት በክቡር ደሙ ዓለምን ለዋጀበትና ለመላው የሰው ዘር ሰላምን ላደረገበት ለመስቀል የምትሰጠው ክብርና ልዕልና ከሌላው ዓለም የላቀና የተለየ ነው፡፡

ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ የጋሞ እናቶች በመስቀል አደባባይ ሳያቋርጡ በየዓመቱ የጋሞኛ ዝማሬ እና ትርዒት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ። ቀ2018 ዓ.ም በዝማሬ ለማገልገል ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል፣ በቤተ ክርስቲያን አማካይነት በዓመት ውስጥ ለአምስት ጊዜያት ያህል በዐደባባይ ትዘክረዋለች፤ ታከብረዋለች፡፡ በመስከረም ወር ብቻ ለዐራት ጊዜ ያኸል ይከበራል፡፡ መስከረም 10 ቀን ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ከስናር ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡበት ዕለት ከ1966ዓ.ም. በፊት የዐፄ መስቀል በዓል ተብሎ በቤተ መንግሥት በታላቅ ሥነ ሥርዓት ይከበር ነበር፡፡

መስከረም 16 ቀን ንግሥት ዕሌኒ በዕጣን ጢስ አመልካችነት አስቆፍራ ከተቀበረበት ያስወጣችበት የመታሰቢያ ዕለት የደመራ በዓል
በማግስቱ መስከረም 17 ቀንም ቅዳሴ ቤቱ መስከረም 21 ቀን ደግሞ፣ ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም የገባበት ዕለት፣ መጋቢት 10 ቀንም፣ ንግሥት ዕሌኒ በመጀመሪያ መስቀሉን ያገኘችበት ዕለት በውዳሴ፣ በቅዳሴ፣ በሥርዓተ ንግሥ ደረጃ በቤተ ክርስቲያን ይከበራል።

17/09/2025

➾ የሞትን ደብዳቤ ወደ ህይወት የቀየረ ቅዱስ ሚካኤል
‎አፎምያን ከሰይጣን ያዳነ ቅዱስ ሚካኤል
‎ገናና የሆነ የመላእክት አለቃ
‎ቅዱስ ሚካኤል ልመናውና አማላጅነቱ ፈጽሞ ይጠብቀን፡፡ ከጽኑ ጠላት እጅ በክንፎቹ ጋርዶ ይሰውረን፡፡ ለዘለዓለሙ አሜን 😍🙏❤

ነሐሴ 19/2017   👉በስመ   አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን   ለምናመሰግንበት ለመልአኩ   ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን           እኔ  #በእግዚአብ...
25/08/2025

ነሐሴ 19/2017

👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን ለምናመሰግንበት ለመልአኩ ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን

እኔ #በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው #ገብርኤል ነኝ
ሉቃ.1፥19

👉ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ዘመኑ ጣኦት የሚመለክበት ንጉስ ናቡከደነፆር በባቢሎን ምርኮ የወሰዳቸው #የእግዚአብሔር ሰዎች አናንያ፤ አዛርያ፤ ሚሣኤል እጅግ ይወዳቸው ነበር

👉ከባቢሎናውይን ይልቅ በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ሦስት ሰፍሮ በምናገኘው ታሪካቸው እንደሚግረን ንጉሱ የጣኦት ምስል አሰራ በገሊላ አውራጃ ያለውን ሕዝብ ጠርቶ ለጣኦቴ ያልሰገደ ወደ እሳት ውስጥ ይጣላል ብሎ አወጀ የንጉስ ትዕዛዝ ነውና ሕዝቡ ሁሉ ለጣዖቱ ሲንበረከክ እነርሱ ግን ቆመው ያዩ ነበር

👉ናቡከደነፆር እርሱ ላስቆመው ጣኦት አለመስገዳቸውን ሲሰማ ተናደደ፤ ተበሳጨም እሳቱን 7 እጥፍ እንዲነድ አስደረገ ሦስቱንም አስሮ እሣቱን እያሳየ "ከመቃጠል ወይስ ለእኔ ጣኦት መስገድ የቱ ይሻላል?" ቢላቸውም #የእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምንም ነገር አያስፈራውምና የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶን ሊያድነን ይችላል ባያድነንም ግን አንተ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም አሉት

👉በዚህ ጊዜ ጉልበት ያላቸው ሠዎች ተፈልገው ሦስቱን ወጣቶች አስረው ወደ እሳት ቶን ውስጥ ጣሏቸው አስረው የጣሉቸው ወታደሮች የእሳቱ ወላፈን አቃጠላቸው ግን መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አበረደላቸው አጠፋላቸው

👉በዚህም ጊዜ ንጉስ ናቡከደነፆር እንዲህ በማለት መሰከረ "እኛ አስረን የጣልናቸው ሦስት ነበሩ አሁን ግን አራተኛው ሰው በእሳቱ ሲመላለስ ይታየኛል የአራተኛው መልክ ደግሞ #የአማልክትን መልክ ይመስላል አለ #የእግዚአብሔር የማዳኑ ስራ ሲገለጥ ቅዱስ ገብርኤል ሲታይ አዋጁ ሁሉ ተሻረ ጉልበት ሁሉ ለጣኦት ይስገድ ተብሎ የነበረው አዋጅ ተሽሮ ጉልበት ሁሉ ለሠለስቱ ደቂቅ አምላክ የሚል አዋጅ ታወጀ

👉የስሙ ትርጓሜ ታማኝ አገልጋይ የሆነው በዘመናችንም ለበርካቶች ታላቅ ተአምራት ሰርቷል ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ጥበቃው ረድኤት በረከቱ አይለየንና ገዳማውያን አባቶችና እናቶች እንደ ባቢሎን እሳት በነደደው ስጋዊ ፍላጎት ውስጥ አሸናፊ እንዲሆኑ የሚረዳቸውም ነው ገዳማውያኑ ሲሉትም በረከታቸው አብሮን እንዲሆን ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናፅና የቅዱሳን አባቶቻችን አበዉ #ሐዋርያት ምልጃ ፀሎታቸው ከኛ ጋራ ይሁን "አሜን"

በአርባ ምንጭ ደብረ ሎዛ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የትንሳኤና ዕርገት በዓል ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ስነስርዓት ተከ...
22/08/2025

በአርባ ምንጭ ደብረ ሎዛ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የትንሳኤና ዕርገት በዓል ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ስነስርዓት ተከበረ።
===========
ነሐሴ ፲፮ ቀን ፳፻፲፯ ዓ/ም የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት ሚዲያ አርባ ምንጭ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የትንሣኤና ዕርገት በዓል በአርባ ምንጭ ደብረ ሎዛ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ነሐሴ ፲፮ ቀን ፳፻፲፯ ዓ/ም በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።

በዓሉ በአርባ ምንጭ እና በአካባቢዋ ከሚገኙ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ደስታና መንፈሳዊ ድባብ የተከናወነ ሲሆን

በበዓሉ ላይ የጋሞና አካባቢው የጎፋና ባስኬቶ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ የሀገረ ስብከታችን የሥራ ክፍል ኃላፊ የሆኑት መጋቤ ሰናያት ያዕቆብ ደስታ ዋና ጸሐፊ፣መልአከ ገነት አባ ወልደ ማርያምየሰበካ ማደራጃ ክፍል ኃላፊ፣ ቀሲስ ደጉ አልቤ የሒሳበሰና በጀት ክፍል ኃላፊ ፣ የደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና የደብረ ሎዛ ቅድስት ኪዳነ ምህረት የሁለቱ አድባራት አስተዳዳሪ የሆኑት ገዳሙ ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።

በዓሉ በድምቀትና በግርማ ሞገስ የተከበረ ሲሆን፣ የቤተ ክርስቲያኗ መዘምራን ያሬዳዊ ዝማሬዎችን በማቅረብ የመንፈሳዊውን በዓል ውበት አድምቀውታል። ምዕመናንም በታላቅ ደስታና ፍቅር የዕለቱን ትምህርተ ወንጌል፣ ስብከት እና ዝማሬ በመካፈል እያሳለፉ ቆይተዋል።

የእለቱ ትምህርት በመልአከ ገነት አባ ወልደ ማርያም በሀገረ ስብከታችን የገዳማትና ሰበካ ማደራጃ ክፍል ኃላፊ ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በዕለቱ ለምዕመናን የመንፈሳዊ በዓሉን ትርጉም የሚገልጽና ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም በእረፍቷ ፣ በትንሳኤዋና በዕርገቷ ዙሪያ በሰፊው ትምህርት ሰጥተዋል። የእመቤታችን ትንሣኤ እና ዕርገት ለሁላችንም የተስፋ ምልክት እንደሆነ ገልጸዋል።

በመጨረሻም በብፁነታቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የእለቱ መርሃ ግብር በጸሎት ተጠናቋል።

🌹ወዳጄሆይ፣ ሁለንተናሽ ውብ ነው።ነውርም የለብሽም።ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ።ከአማና ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖርያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።እኀቴ ሙሽራዬ ሆይ፣...
15/08/2025

🌹ወዳጄሆይ፣ ሁለንተናሽ ውብ ነው።
ነውርም የለብሽም።
ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ።
ከአማና ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖርያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።
እኀቴ ሙሽራዬ ሆይ፣ልቤን በደስታ መላሽው በዓይንሽና በአንገትሽ ድሪ ልቤን በደስታ መላሽው።
🌹እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ፣ ፍቅርሽ እንዴት መልካም ነው?
ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እንዴት ይሻላል?
የዘይትሽም መዓዛ ከሽቱሁሉ ይበልጣል
🌹ሙሽራዬ ሆይ፣ ከከንፈሮችሽ ማር ይንጠባጠባል።
እናቴ ማርያም ሆይ ከሚፈታተነኝ ከጠላት ሴራ አድኚኝ
ጥበቃሽ አይለየን አሜን #

ልዑል ማደሪያዉ ትሆኝ ዘንድ መርጦሻልና ምስጋና ይገባሻል በወርቅ የተሸለምሽ የርግብ ክንፍ በብር ያጌጥሽ ምስጋና ይገባሻል። የምስራቅ ደጃፍ የብርሃን እናቱ ላንቺ ምስጋና ይገባሻል። ማርያም ሆ...
13/08/2025

ልዑል ማደሪያዉ ትሆኝ ዘንድ መርጦሻልና ምስጋና ይገባሻል በወርቅ የተሸለምሽ የርግብ ክንፍ በብር ያጌጥሽ ምስጋና ይገባሻል። የምስራቅ ደጃፍ የብርሃን እናቱ ላንቺ ምስጋና ይገባሻል። ማርያም ሆይ ከተመረጡ የተመረጥሽ ከተከበሩ የተከበርሽ ላንቺ ምስጋና ይገባሻል። ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን ለምኝልን። አሜን።

እሳቱ ጠፋ።ብዙዎቻችንን ያስደነገጠው ይልቁንም የቤተክርስቲያን ጉዳይ የሚያሳስባቸው ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ሊቀጳጳስ በተገኙበትበኦቶና ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም የላሜራ ሱቆች ላይ የተነሳው ድን...
12/08/2025

እሳቱ ጠፋ።
ብዙዎቻችንን ያስደነገጠው ይልቁንም የቤተክርስቲያን ጉዳይ የሚያሳስባቸው ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ሊቀጳጳስ በተገኙበት
በኦቶና ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም የላሜራ ሱቆች ላይ የተነሳው ድንገተኛ የእሳት አደጋ በእግዚአብሔር ቸርነት በቁጥጥር ሥር ሆኗል ።ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ።

Address

Arbaminch
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጋሞ እና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ሰብከት በደራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት መነና ቅ/ሚ/ቤ/ክ/ማ ገጽ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category