Wubalem Construction

Wubalem Construction Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wubalem Construction, Real Estate, Ghiorghis, Bahir Dar.

24/01/2026

👉ብሎኬት /hollow concrete block /
⏩Hollow Concret Block (HCB) ወይም የግድግዳ ብሎኬት/Wall HCB/ በመባል ይታወቃል።
*የብሎኬት ምርት ሲደረግ ጠቀሜታው ለሁለት ጉዳይ ነው
1. ሸክም መቌቌም የሚችል/Load Bearing/
2. ሸክም መቌቌም የማይችል /Non-Load Bearing/
*ይሄንን መሰረት ያደረገም የደረጃ ክፍፍል/Class/ ይኖራቸዋል።
*ሸክም መቌቌም የሚችሉት ብሎኬቶች "ክላስ ኤ እና ቢ" /
Class A and B/ በመባል ሲመደቡ ሸክም መቌቌም
የማይችሉት የብሎኬቶች ደግሞ "ክላስ ሲ" /Class C/ በመባል
ይመደባሉ።
➡ብሎኬት በተለምዶ በመጠናቸው ባለ10፣ ባለ15 እና ባለ 20 በመባል ይለያሉ::
ርዝመት x ስፋት x ቁመት/ Length x width x depth/
ማለትም Standard Dimenssion
*40x20x20cm
*40x20x15cm
*40x20x10cm
➡እያንዳንዱ ብሎኬት ሸክም የመቌቌም አቅማቸው
በሜጋ ፓስካል(Mpa) ይለካል
*Note:
1 kilogram per square centimetre = 0.0981 mega pascal

*Class A=3.8mpa
*Class B=3.2mpa
*Class C=1.8mpa .

18/07/2025

👉ለጠቅላላ እውቀት... ከተመቻቹ እና እንዲቀጥል ከፈለጉ አጋሩ!

Q1. What is the Unit Weight of concrete?

answers:- The unit weight of concrete depends on the type of aggregates and amount of voids. As per IS : 456-200 Unit weight of PCC is 24KN/m3 and RCC is 25KN/m3

Q2. What is the unit weight of Steel?

answers:- The unit weight of Steel is 78.5KN/m3

Q3. What are the Nominal Concrete Mix proportions
for different grades?

answers:- Important: C-15 - 1:2:4 and C-5 - 1:4:8,C-20 and C-25 - 1:2:3 (Cement:Sand:aggregate)

Q4. What is ductility?

answers:- Ductility is the Ability to deform under tensile
stress.

Q5. How to find the weight of steel bar used in reinforcement?

answers:- Weight of Bar in kg/m = Dsquare/162.2 D- Dia of bar in mm

Q6. What’s the difference between one-way slab
and two-way slab?

answers:- One way slab: Ratio of Longer Span / Shorter
span > 2 Two way slab: Ratio of Longer span/ shorter span

18/07/2025

ለዛሬ🤔

⭐️To compute the area of the footing required for the column, we need to determine the total load acting on the column and then use the soil bearing capacity to find the required area.

1. Total Load on the Column:
- Live Load = 250 kN
- Dead Load = 600 kN
- Total Load (P) = Live Load + Dead Load = 250 kN + 600 kN = 850 kN

2. Soil Bearing Capacity (SBC):
- SBC = 200 kN/m²

3. Area of the Footing (A):
The area required can be calculated using the formula:

- Soil Bearing Capacity (SBC): 200 kN/m²
- Required Area (A):( A = {P}/{SBC} = 850/kN200kN/m^2 = 4.25m^2

Therefore, the area of the footing required is 4.25 m²

18/07/2025

👉የ ዛሬ ርዕስ

💫1. የለውጥ (variation) እና የተጨማሪ (supplementary) ሥራዎች አንድነት እና ልዩነት መግለጽና እንዲሁም ሁለቱ የሥራ ትዕዛዞች ውስጥ መካተት ያለባቸው የስራ አይነቶች ምን አይነቶቹ ናቸው? እንዲሁም በንድፍ ስራ ወቅት የተዘነጉ እና በግንባታ ሂደት የሚታዩ የስራ ክፍተቶች እስከ ምን የገንዘብ መጠን ድረስ በጀቱን በማስተካከል በነባሩ የውል ሰነድ ሊሰሩ ይችላሉ?

🚧1.1) የለውጥ ሥራዎች (Variation Works) ማለት የንድፍ ስራዎች የተሰሩለት የግንባታ ፕሮጀክት ሥራ ላይ በመጠን ልዩነት የሚፈጠር የስራ አይነት ማለት ነው፡፡

⏺ይህም የስራ አይነት ምንም የዋጋ ድርድር ሳይሰራለት በዋናው ውል ላይ የተገለጸውን የዋጋ መጠን (rate) መሰረት በማድረግ የሚሰራ የስራ አይነት ነው፡፡

⏺በግዢ ኤጀንሲ መመሪያ አንቀጽ 15.1 መሃንዲሱ ግንባታ ስራዎችን በተገቢው መንገድ እንዲያጠናቅቅ መይም በጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ በየትኛወም ግንባታ የሥራ ክፍል ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ትዕዛዝ የመስጠት ሥልጣን አለው፡፡

⏺ማሻሻያዎቹ ግንባታ መጨመርን፣ መተውን፣ መተካትን፣ የጥራት ብዛትን ቅርፅን፣ ባህሪን፣ አይነትን፤ ቦታን፣ ልኬትን፣ ከፍታ ወይንም የመስመር ለውጦችን እና በተጠቀሰው ቅደም ተከተል ወይም ዘዴ በሚፈጸም ጊዜ የግንባታ ሥራዎች ለውጦችን ያካትታሉ፡፡

⏺ምንም ዓይነት የማሻሻያ ትዕዛዝ ውሉን ውድቅ ሊያደርግ አይችልም፤ ነገር ግን ሁሉም ማሻሻያዎች በውል ዋጋ ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ ካለ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 15.5 እና 15.7 ሥራ ዋጋዎቹ መገመት ይኖርባቸዋል፡፡

🚧1.2) በገንዘብ ሚንስትር የፌዴራል መንግሥት የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ክፍል አራት አንቀጽ 70/2/ሀ/ መሰረት በለውጥነት የሚታዘዘው ዕቃ፣ የምክር አገልግሎት ወይም የሌሎች ግዥዎች መጠን ከውሉ ጠቅላላ ዋጋ 25% መብለጥ የለበትም ይላል፡፡ እንዱሁም በአንቀጽ 70/2/ለ/ በፊደል “ሀ” መሰረት ተጨማሪ ግዥ ለማዘዝ የቀድሞው ግዥ ውል ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ወይም ውሉ ከተጠናቀቀበት ቀን አንስቶ በሚቀጥሉት 9 (ዘጠኝ) ወራት ጊዜ ውስጥ መሆን አለበት፡፡ በአንቀጽ 70/2/ሐ/ መሰረት ደግሞ ግዥ ሲፈጸም በመጀመሪያው ውል ከነበረው የነጠላ ዋጋ የበለጠ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይፈቀድም፤ እንዲሁም 70/2/መ/ ከላይ በፊደል "ሐ" የተቀመጠው ቢኖርም የመጀመሪያው ውል የዋጋ ማስተካከያ የሚፈቅድ ከሆነ እና የዋጋ ማስተካከያ የተደረገ ከሆነ የለውጥ ስራው በተስተካከለው ዋጋ መሰረት ይሆናል፡፡ ጠቅለል ሲደረግ ከላይ የተገለጹትን ሁኔታዎች መሟላታቸውን አረጋግጠው ሥራ በሚሰራበት ጊዜ እና በንድፍ ሥራዎች ወቅት ያልታሰቡ ሥራዎችን በመጀመሪያው ውል ውስጥ ያልተካተቱ የለውጥ ሥራዎችን ማሠራት ይችላሉ፡፡

🚧1.3) የተጨማሪ ሥራዎች (Supplementary Works) ማለት በንድፍ ወቅት ያልታዩ ሥራዎች ነገር ግን በግንባታ ወቅት የታዩ ሥራዎችን ግንባታ በሚሰራው ተቋራጭ ለማሰራት በአዲስ ውል እና ዋጋ የሚሰሩ ስራዎች ናቸው፡፡

🚧1.4) የተጨማሪ ሥራዎች በገንዘብ ሚንስትር የፌዴራል መንግሥት የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ክፍል አራት በአንቀጽ 70/3/ሀ/ መሰረት በተጨማሪነት ወይም በዋናው ሥራ ላይ ያልነበሩ ሥራዎች በማሻሻያነት የሚታዘዘው የግንባታ ሥራ የገንዘብ መጠን ከመጀመሪያው ውል ጠቅላላ ዋጋ ከ30% የበለጠ መሆን የለበትም፡፡

⏺እንዲሁም በአንቀጽ 70/3/ሀ/ የመንግስት መ/ቤቱ በተጨማሪነት እንዲሰሩ የታሰቡት የግንባታ ሥራዎች በመጀመሪያው ውል ውስጥ መካተት ይገባቸው የነበሩ እና ሥራዎቹን ነጣጥሎ ማሰራት ለአፈፃፀም አአስቸጋሪ ወይም የመ/ቤቱን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚጎዱ መሆኑን የሚመለከተው አስፈጻሚ አካል ማረጋገጥ አለበት፡፡

⏺በአንቀጽ 70/3/ሐ/ በተጨማሪነት የሚታዘዙት የግንባታ ሥራዎች የነጠላ ዋጋ በውል ውስጥ ሊገኝ የሚችል ከሆነ የተጨማሪው ስራ በውል ውስጥ ባለው ነጠላ ዋጋ መሰረት ወይም የዋጋ ማስተካከያ የተደረገ ከሆነ በተስተካከለው ዋጋ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

🚧1.5) የነጠላ ዋጋው ውል ውስጥ የማይገኝ ከሆነ በድርድር ስምምነት ላይ የሚደረስበት ዋጋ የገበያ ዋጋ መሆኑን መ/ቤቱ ማረጋገጥ አለበት፡፡

▶️በተጨማሪ የግንባታ ሥራው ምክንያት አለመግባባት ቢፈጠር በከተማና ልማት ሚንስትር (MoWUD) አንቀጽ 52 መሰረት በኢንጅነሩ ትዕዛዝ የተጨማሪ ሥራዎች እና የለውጥ ሥራዎች በውሉ ውስጥ በተቀመጡት ዋጋዎች ልክ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

⏺በኢንጅነሩ አስተያየት በዋጋ መደራደሪያ ሰነዱ ላይ ዋጋዎቹ ተመሳሳይነት ያለው ካልሆነ፤ አዲሱ ውሉ ለልዩነት ወይም ለተጨማሪ ሥራዎች ተፈጻሚነት ያላቸውን ዋጋዎችን ካልያዘ ተስማሚ ያልሆኑ ተመኖች ወይም ዋጋዎች አለመግባባቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ መሃንዲሱ በእሱ አስተያየት ምክንያታዊ እና ትክክለኛ መሆን ያለባቸውን ዋጋዎችን መወሰን ይኖርበታል ይላል፡፡

18/07/2025

👉Why is vibration Important in Concrete works?

🚧Concrete vibration is a critical process in construction that ensures the quality, strength, and durability of concrete structures.

⏺Proper vibration removes entrapped air, improves compaction, and enhances the overall performance of hardened Vibration.

💫1. Elimination of Air Voids:

⏺Fresh concrete contains air voids that, if not removed, can significantly reduce its strength and durability.
⏺Vibration helps eliminate these voids by allowing the concrete to settle and compact properly.
⏺This enhances the concrete’s density, leading to increased strength.

💫2. Improved Bond with Reinforcement:

⏺For reinforced concrete structures, achieving a strong bond between the concrete and steel reinforcement is essential. ⏺Poor compaction can lead to gaps around reinforcement bars, reducing the structural performance.
⏺Vibration ensures that concrete fully encases the reinforcement, improving adhesion and load transfer.

💫3. Enhanced Durability:

⏺Concrete with air pockets and improper compaction is more prone to cracks, water pe*******on, and chemical attacks.
⏺Vibration compacts the concrete effectively, making it more resistant to environmental factors, thereby increasing its lifespan.

💫4. Better Surface Finish:

⏺In applications requiring a smooth and aesthetically pleasing surface, such as fair-faced concrete or architectural finishes, vibration plays a crucial role.
⏺Proper vibration minimizes surface defects like honeycombing and segregation, resulting in a uniform, visually appealing finish.

💫5. Increased Load-Bearing Capacity:

⏺Well-compacted concrete has higher compressive strength, which translates into greater load-bearing capacity. ⏺This is crucial for high-rise buildings, bridges, and other critical structures where strength and stability are paramount.

💫6. Prevention of Segregation and Bleeding:

⏺Excess water and improper compaction can lead to segregation, where coarse aggregates settle at the bottom, and water rises to the surface (bleeding).
⏺Controlled vibration helps maintain a homogeneous concrete mix, preventing such defects.

📜The best Practices for Concrete Vibration:

🏷To achieve optimal results, it's essential to follow best practices when vibrating concrete:

✔ Use the right equipment – Internal vi*****rs (poker vi*****rs) and external vi*****rs should be selected based on the type of concrete work.
✔ Control vibration time – Over-vibration can cause segregation, while under-vibration leaves voids. Typically, 5-15 seconds per insertion is sufficient.
✔ Proper spacing – Vi****or insertion points should be evenly spaced (typically 30-50 cm apart) to ensure uniform compaction.
✔ Avoid touching formwork and reinforcement – Excessive vibration against formwork can lead to leakage, and direct contact with rebar may cause displacement.

18/07/2025

👉" የግንባታ ደረጃዎች "
"Building Construction Classification"

⭐️በሊዝ የተያዘ መሬት ላይ ግንባታ የመጀመሪያ እና የማጠናቀቂያ ቀነ ገደብ እንደ ግንባታዎቹ ደረጃ ተለያይቶ ተቀምጧል (በሚቀጥለው ክፍል ይዳሰሳል)።

📜ለዛሬው የግንባታ ደረጃዎ አከፋፈልን እንመልከት።

⏺የሀገራችን የኮንስትራክሽን ሕግ ግንባታዎችን በሦስት (3) ዋና ዋና መደብ ይከፍላቸዋል።

🎲እነሱም፦ አንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች፣ መካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች፣ እና ከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች ናቸው።

💫A. አነስተኛ ደረጃ ግንባታዎች (Small scale constructions)

አነስተኛ ደረጃ ግንባታዎች የሚባሉት እስከ ሦስት ወለል ያላቸው የተናጠል መኖሪያ ቤቶች (private residential building) ወይም እስከ ሦስት ወለል ያላቸው የሕዝብ መጠቀሚያ ያልሆኑ ሌሎች ግንባታዎች ወይም የይዞታ ስፋቱ እስከ 250 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚገነቡ ግንባታዎች ናቸው።

💫B. መካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች (Intermediate scale constructions)

መካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች የሚባሉት 5 ወለል እና ከዚያ በታች የሆኑ የሕዝብ መጠቀሚያ ሕንጻዎች፣ ወይም የይዞታ ስፋቱ ከ251 ካሬ ሜትር እስከ 5000 ካሬሜትር ይዞታ ላይ የሚገነቡ ግንባታዎች፣ ወይም የመኖሪያ ቤት ባለ 4 እና ባለ 5 ወለል የሆኑ ግንባታዎች፣ ወይም የመኖሪያ ቤት በአንድ ጊዜ እስከ 80 ነጠላ ቤቶች የያዙ ግንባታዎች፣ ወይም የሕዝብ መጠቀሚያ ያልሆኑ ሌሎች ወለላቸው ባለ 4 እና ባለ 5 የሆኑ ግንባታዎች፣ ወይም ለትምርት ተቋማት እስከ 2ኛ ከፍተኛ ደረጃ የሚያጠቃልሉ ግንባታዎች፣ ወይም ለቤተ መጻሕፍትና ለሁለገብ አዳራሾች እስከ 500 ሰው የሚይዙ ግንባታዎች፣ ለጤና ማዕከል እስከ ከፍተኛ ክሊኒክ የሚያጠቃልሉ ግንባታዎች፣ ለስፖርት ሜዳዎች እና ለስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት እስከ 500 ሰው የሚይዙ ግንባታዎች፣ ወይም በአጠቃላይ የወጪ ግምታቸው እስከ ብር አምስት ሚሊዮን (5,000,000) ብር የሆኑ መካከለኛና አነስተኛ የማምረቻ እና ማከማቻ ተቋማትን ያጠቃልላል።

💫C. ከፍተኛ ግንባታዎች (High scale constructions)

ከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች የሚባሉት ባለ ስድስት (6) ወለል እና ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ግንባታ፣ ወይም የይዞታ ስፋቱ ከ5000 ካሬሜትር ቦታ በላይ የሆነ ይዞታ ላይ ለሚገነቡ ወይም በዓለም በሀገር እንዲሁም በከተማ አቀፍ ደረጃ ለሚገነቡ የትራንስፖርት የመናኸሪያ ተቋማቶች፣ ወይም ትላልቅ የዲፕሎማቲክ ተቋማት የሚገነቧቸው ግንባታዎች፣ ወይም ከላይ በአነስተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ከተጠቀሱት ውጪ ያሉ ግንባታዎችን ያጠቃልላል።

18/07/2025
ሰላም እንዴት ናቹ እንኳን ለ2017  አደረሳቹ
11/09/2024

ሰላም እንዴት ናቹ እንኳን ለ2017 አደረሳቹ

11/09/2024

ሰላም እንዴት ናቹ እንኳን ለ2017 አደረሳቹ

18/09/2021

ሰላም እንዴት ናቹ እንኳን ለ2014 አደረሳቹ
🚧በኮንስትራክሽን ስራ ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ
ኢንጅነርዎች ሊያውቃቸው የሚገቡ 10 ወሳኝ ነጥቦችን ይዘን ከች ብለናል መልካም አዲስ አመት
1) የግንባታ እቃዎች ፍተሻ( TESTS OF BUILDING
MATERIALS) አንድ ጥሩ ኢንጅነር በሳይት ላይ የሚሰሩ
የግንባታ እቃዎችን ለመፈተሽ
የሚጠቅሙ የፍተሻ ስራዎችን የግድ ማወቅ ይጠበቅበታል።
ከታች የተለያዩ
አይነት የፍተሻ ቴክኒኮች ተጠቅሰዋል
የኮንክሪት ፍተሻ(Concrete Test):
•Slump test,
•compression test (cubic or cylindrical test),
•split tensile test, soundness etc.
የአፈር ፍተሻ (Soil Test):
•Core cutter test,
•compactiontest,sand replacement test, triaxial test,
consolidation test etc.
Bitumen Test:
•Ductility test, softening point
test, gravity test, pe*******on test etc.
(በእርግጥ እነዚህን ሁሉ እውቀቶች በየዮንቨርስቲዎች ውስጥ
አንማር ይሆናል
ነገር ግን ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የግድ
መማር
ማወቅ አለብን ዩ ቲዩብ ገብተን ብንፈልግ በቪድዮ የተደገፉቁም
ነገሮችን እናገኛለን ጥቆማችን ነው ::
:
2) የአፈር ጥናት (INVESTIGATION OF SOIL)
የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮችን ተጠቅመን የአፈሩን የመሸከም
አቅም እና
ርጉእነት (settlement and stability ) የምንገነባው አካል
ከመገንባቱ በፊት ልናውቅ እንችላለን።
እንደ ኢንጅነር የአፈር ጥናት ለማድረግ የሚጠቅሙ
በሳይት ላይ የሚከወኑ የፍተሻ ቴክኒኮችን ማወቅ ግዴታችን ነው።
:
3 የተለያዩ የሰርቬይን መሳሪያዎች አጠቃቀም ማወቅ(USES OF
SURVEYING INSTRUMENTS)
በእርግጥ በብዙ የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ራሱን የቻለ
የሰርቬይ ባለሞያ መቅጠር አሁን አሁን የተለመደ ቢሆንም ነገር
ግን መሰረታዊ የሚባሉ የሰርቬይ
መሳራያዎች ለምሳሌ ቶታል ስቴሽን እና ቴዎዶላይት
አጠቃቀማቸውን አንድ ኢንጅነር የግድ ማወቅ አለበት። የግድ !
:
4). የተለያዩ የግንባታ ስታንዳርድ ኮዶች (STANDARD CODES
USED IN CONSTRUCTION)
ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ከመልካ ምድራቸው
የአየር፣የንፋስ፣የመሬት መንቀጥቀጥ ከባቢያዊ ፀባያቸው አንፃር
የሚያዘጋጁት የግንባታ መርህ
(Construction codes) አላቸው።
አንድ ኢንጅንየር ግንባታ የሚያደርግበት ሃገርን ስታንዳርድ ኮድ
የማወቅ ግዴታ አለበት ምክንያቱም የሚገነባው ቁስሃገሪቱ ባላት
ተፈጥሯዊ መሰናክል እንዳይሰናከል እና እንዳይወድም። እነዚህን
ኮዶች ወይም መመሪያዎች ሳይከተል የሚገነባ የትኛውም ግንባታ
የመፍረስአቅሙ በእጥፍ የጨመረ ነው።

5) BAR BENDING SCHEDULE
ባር ቤንዲንግ ስኬጁል ለኢንጅነየሮች ጠቃሚ የሆነ ቻርት (በተለይ
ኮንስትራክሽኑ ሬንፎርስመንት ካለው)። ይህ ቻርት ሬንፎርስድ
የሆነው የግንባታ
አካል ማለትም ቢም፣ኮለን፣ስላብ፣ዋል...የሚጠቀማቸውን ቤረቶች
የሚቆረጥበት ርዝመት ፣ በምን ያህል ርዝመት እንደሚታጠፉ እና
ምን ያክል ተመሳሳይ እጥፋትና ርዝመት ያላቸው ባሮች በዛ አካል
ውስጥ እንደሚኖሩ በግልፅ ይነግረናል ።
ይህ ቻርት ብረትን ያለብክነት እንድንጠቀም እና የስትራክቸሩን
ደህንነት (safety) እንድንጠብቅ ይጠቅመናል

6) የንድፍ እና ዲዛይን ንባብ (DRAWING AND DESIGN)
አንድ ሳይት ኢንጅነር ከምንም ከምንም በላይ የግንባታን ንድፍ
የማንበብ በጣም ትልቅ እውቀት ሊኖረው ይገባል።

Address

Ghiorghis
Bahir Dar

Telephone

+251921244684

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wubalem Construction posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wubalem Construction:

Share

Category