sofi Habshewet

sofi Habshewet Informations de contact, plan et itinéraire, formulaire de contact, heures d'ouverture, services, évaluations, photos, vidéos et annonces de sofi Habshewet, Immobilier, Democratic Republic of the.

27/12/2023
የአፋልጉኝ  ጥሪሼር በማድረግ እንተባበር አማርኛ አላውቅም ተጨንቄያለሁ ልጄ ከጠፋች 10 ቀን አለፋት ያልሄድንበት ፖሊስ ጣቢያ የለም ልናገኛት አልቻልንም ይላሉ ሶሪያዊው ስደተኞች ወላጅ አባት...
14/08/2023

የአፋልጉኝ ጥሪ

ሼር በማድረግ እንተባበር

አማርኛ አላውቅም ተጨንቄያለሁ ልጄ ከጠፋች 10 ቀን አለፋት ያልሄድንበት ፖሊስ ጣቢያ የለም ልናገኛት አልቻልንም ይላሉ ሶሪያዊው ስደተኞች ወላጅ አባት እና ወላጅ እናት

ሀምሌ 29 /11/ 2015 ቅዳሜ ቀን ከቀኑ 11 ሰዐት አካባቢ ቦሌ ሩዋንዳ ጫት ተራ ሰፈረረ ሽቶ ስትሸጥ መታየትዋን ወላጆችዋ እምባ እየተናነቃቸው ይገልፃሉ
ይቺ እህታችን ኒቃብ ለባሽ ነች በወቅቱ ከቤት ስትወጣም ኒቃብ ለብሳ ነበር ።

ወደ ኢትዮጲያ ከመጣች ገና ሁለት ወሯ ነው በእጇ ላይ ምንም አይነት ዶክመንት አልያዘችም ስሟ ሱዛና ሙሀመድ ረሺድ ወይም በቅጥል ስሟ (ረዋን) ትባላለች ።

ያያት ሰው በዚህ የወላጅ አባቷ ስልክ በአረብኛ ለምታወሩ

0 94 402 9994

ወይም በዚህ በአማርኛ ለምታወሩ ጥቆማ ሰጡን ጀዛኩሙላህ ከይር
0991767935

ሼር በማድረግ እንተባበር

10/08/2023

الحمد الله
Alhamdulillah

አልሃምዱሊላህ
የማይነጋ ለሊት የለም
የማያፍ ቀን የለም

«.አምሓራ » ከሌሎች ህዝቦች ጋር ሆኖኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ይዞ የኖረህዝብ ነው። ለዚች ሃገር ደሙን አፍስሷል፣ አጥንቱን ከስክሷል። የኔ ብሎ ስለሚላት ሀገሩ ሲዋደቅ፣ ከጠላት ሲተናነቅ፣...
09/08/2023

«.አምሓራ » ከሌሎች ህዝቦች ጋር ሆኖ
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ይዞ የኖረ
ህዝብ ነው። ለዚች ሃገር ደሙን አፍስሷል፣ አጥንቱን ከስክሷል። የኔ ብሎ ስለሚላት ሀገሩ ሲዋደቅ፣ ከጠላት ሲተናነቅ፣ ሩኋን እንደማህተብ በአንገቱ አስሮ ስትቸገር እየተቸገረ፣ ስታብብ እየደመቀ ኖሯል። ከምንም በላይ ይወዳታልና የኢትዮጵያ ነገር ወንዝ አላሻግር እያለው፣ መሃላ ግዝት ሆኖ እየፈቀደው በስሟ የመጣን ሁሉ እንደቸር ነጋሪ፣ እንደበጎ ቀማሪ እያመነ ሲከተል ኖሯል።

በዚህም መከራ ታግሷል። ያለአበሳው ስሙ ሲጠፋ፣ ታሪኩ ሲጎድፍ ችሎ አሳልፏል። ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትንና የአንድ ጥላ ሰብሳቢነትን አምኖ በመከራ ጸንቷል።

ለአማራ ኢትዮጵያ እዳው ነች። እንዳይተዋት እርሙ፣ በጉያው እንዳትቆይ ደግሞ የመዳፍ ላይ ፍም ሆና ለዘመናት ቆየች። ለአማራ ኢትዮጵያዊነቱም መከራው፣ እሱን ትቶ አማራነቱም ፈተናው ሆነ። ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲል አሐዳዊ ነው፤ አማራ ነኝ ሲል ጽንፈኛ ነው። ሐገሬ ሲል ያላነገሳቸውን "የአጼው" ወገንተኛ ይደረጋል። ቀዬዬ፣ ዘውጌ ሲል ደግሞ “የሌላው” ስጋት ይሆናል። ይሄንን ታግሶ እያስታመመ ኖረ።

በየጊዜው የሚነሱ መንግስታት አጋዙት፣ ገረፉት፣ አፈናቀሉት፣ ገደሉት። በቆንጨራ ተመተረ፣ ወደገደል ተወረወረ፣ ቤቱና ንብረቱ በላዩ ላይ ነደደ፣ ሚስቱና ልጆቹ ተደፈሩ፣ ደሙ ፈሰሰ፣ ሰብሳቢ እንደሌለው እንደወጣ ቀረ። በቀዬው እንዳይማር በመሰሪ ትርክት ተቀይዶ በገዛ ልጆቹ ጭምር ከታሪክ ተሰውሮ፣ ከአለም ተገልሎ፣ በታቀደ ብልሐት በዘዴ ደኸዬ። በድንቁርና አለንጋ ለበለቡት። የታሪክ፣ የስልጣኔ አውራ የነበረ ህዝብ የኋላቀርነትና የበሽታ ምልክት ሆነ። ሸማ ይለብስ የነበረ ኩሩ በቁምጣና "በአዘነ" የተሰየመ ንኡስ ስንኩል ተደረገ።

አሁን ያ ጊዜ እያበቃ ነው። እንደቡግንጅ የምትነዝገው ህማሙን ቆርጦ ይጥላታል። ከሁሉም ህዝብ እኩል ሆኖ ይቆማል። መብቱን ድምጹን ሊያፍኑ የሚሞክሩ አይችሉትም። በመሰሪነት አንገቱን ጨምድደው የያዙትን በጠንካራ ክንዱ ይሰብራቸዋል። በአማራ ደም ብቻ የምትቆም ሃገር አትኖርም። ከሌላው ህዝብ የተለየ ሃገር የማቆም የሞራል ግዴታም አይኖረውም። በሃብቱ እኩል እንዲጠቀም፣ ጥላሸት የለቀለቁት ታሪኩም ደምቆ እንዲወጣ፣ ከማንም የማይበልጥበት ከማንም የማያንስበት ሃገር የሚኖር ከሆነ አብሮ ይሰራል። ማንም እየተነሳ እንደፋሲካ በሬ ደሙን አያፈሰም። ልጆቹ አይገደሉበትም። አማራ በመሆኑ አይሳደድም። ሲገፉት ታግሶ ሲነሳ የክንዱን እሳትነት ያሳያል። እበልጣለሁ ብሎ አይታበይም፤ ታንሳለህ የሚሉትን ግን የሚታገስበት ዘመን አብቅቷል። የህዝብ ማእበልን “ጃውሳ”ና “ወንበዴ” ብሎ ስም በማውጣት አያቆሙትም! ደርግም ይል ነበር— አሁን የለም!

አማራ ነን!
ኢትዮጵያ ናት ሃገራችን!
ህዝብ ነው የሚያሸንፍ! (በ Dr ዮናስ አ )

ሱሌማን አብደላ

08/08/2023

😒 Abiy Ahmed Ali ግን ምን አስበህ ነው🤔

Adresse

Democratic Republic Of The

Site Web

Notifications

Soyez le premier à savoir et laissez-nous vous envoyer un courriel lorsque sofi Habshewet publie des nouvelles et des promotions. Votre adresse e-mail ne sera pas utilisée à d'autres fins, et vous pouvez vous désabonner à tout moment.

Partager