Tamagne Hune ታማኝ ሁን

Tamagne Hune ታማኝ ሁን Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tamagne Hune ታማኝ ሁን, Real Estate, Addis Ababa.

15/03/2024
በሬ ከአራጁ ጋር ይውላል የሚባለው ዝም ብሎ እንዳይመስልህ። በሚከተለው ፎቶ አይነት ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሲበዛ የዋህ ናቸው። ከገዳዮቻቸው ጋር በአንድ ወንበር ቁጭ ማለታ...
15/03/2024

በሬ ከአራጁ ጋር ይውላል የሚባለው ዝም ብሎ እንዳይመስልህ። በሚከተለው ፎቶ አይነት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሲበዛ የዋህ ናቸው። ከገዳዮቻቸው ጋር በአንድ ወንበር ቁጭ ማለታቸው ተገቢ አልነበረም። እንደ ጌታቸው ረዳ ያዋረዳቸው፣ ያንቋሸሻቸውና የተሳለቀባቸው እስካሁን በአለም ላይ አልሰማውም።

ቦድካው ጌታቸው ረዳ ትንሽ እንኳ ስቅጥጥ አይለውም የአንድን ታላቅ ሀገር መሪ በዚያ ዱዳ አንደበቱ ስንቱን እንዳላለው ዛሬ በአንድ ጠረጴዛ አብሮ መቀመጥ ሸም ነው።

ዶ/ር አብይ ግን ሙልጭ አድረገው ቢገርፏቸውም የሚያኮርፉ አይመስለኝም። የዋህነት ለበግም አልበጀ። የህወሃት ሰወችን ማመን ሲበዛ ቂልነት ነው።

የምርጥ ስብዕና ባለቤት፣በስራ ታታሪነቱ፣ በአድማጭነቱ፣በሀገር ወዳድነቱና በምርጥ የአመራር ብቃቱ የሚታወቀው ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢፌድሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ለምንወ...
08/02/2024

የምርጥ ስብዕና ባለቤት፣በስራ ታታሪነቱ፣ በአድማጭነቱ፣በሀገር ወዳድነቱና በምርጥ የአመራር ብቃቱ የሚታወቀው ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢፌድሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
ለምንወደውና ለምናከብረው ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንለት እንመኛለን።

31/01/2024
የም/ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት መልቀቃቸው ተገቢ ነው ወይስ ተገቢ አልነበረበትም? እስቲ አስተያየት ስጡበት።
30/01/2024

የም/ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት መልቀቃቸው ተገቢ ነው ወይስ ተገቢ አልነበረበትም? እስቲ አስተያየት ስጡበት።

21/06/2023
13/04/2023

መሪ ማለት ለሚመራው ህዝብ እውነተኛ ታማኝ መሆን ነው!
ታማኝ ሁን

02/04/2023

በየቀኑ እንደ እስስት እየተቀያየሩ ሀገር መምራት አይቻልም።
ታማኝነት ለራስ ነው

ፈጣሪ እድሜና ጤና እንዲሰጠው የሚጸልዩለት እውነተኛ የኢትዮጵያ ልጅ ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አንደኛው ሲሆን ሌሎቹን በቅርብ ቀን እናሳውቃለን።እሸ አንተ ለሀገሬ የምታሰፈልጋት ንጹ ሰው ነህ። ሰ...
16/03/2023

ፈጣሪ እድሜና ጤና እንዲሰጠው የሚጸልዩለት እውነተኛ የኢትዮጵያ ልጅ ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አንደኛው ሲሆን ሌሎቹን በቅርብ ቀን እናሳውቃለን።

እሸ አንተ ለሀገሬ የምታሰፈልጋት ንጹ ሰው ነህ። ሰርቶ መወጥን፣ትህትናን፣ እምነትን፣ ለሠው መኖርን፣ የሰውን ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ እኩል መውደድን አስተምረሃል። ምናለ ሁሉ ከአንተ ቢማር? አምላክ አድሜ ጤናና ብዙ ሀብት ሰጥቶህ የተቸገረ ወገንህን የበለጠ የምትረዳ ያድርግህ። እመ ብርሃን ሁልጊዜ ትከተልህ።

የዘር ማፅዳት ወንጀሉን መንግስታዊ መሆን እነሱም አልደበቁም!ከስር የሚታየው የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራር ነው። ከአዲስ አበባ ጭምር ቤታቸው እየፈረሰ እየተፈናቀሉ ያሉት ንፁሃን እን...
16/03/2023

የዘር ማፅዳት ወንጀሉን መንግስታዊ መሆን እነሱም አልደበቁም!

ከስር የሚታየው የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራር ነው። ከአዲስ አበባ ጭምር ቤታቸው እየፈረሰ እየተፈናቀሉ ያሉት ንፁሃን እንደባይተዋር አይቶ ይውጡልን እያለ ነው። የፃፈው የስራቸውን ውጤት ስለሚኮሩበት ነው። መደበቅ ስለማይችሉ ነው። ንፁሃንን በዚህ መልክ ማሳደድን በአደባባይ በድልነት የሚፅፉት ጉዳይ ሆኗል። የዘር ማፅዳቱን ኮርተው በአደባባይ የሚፅፉበት ነው። የዘር ማጥፋቱን ደረት ነፍተው የሚናገሩለት ነው።

የአማራ ክልል መንግስት ከኦሮሚያ የተፈናቀሉት ይመለሳሉ የሚል መግለጫ ይሰጣል። እነሱ ግን ከአዲስ አበባ ያፈናቅላሉ። ተፈናቃይ ሊመለስ እንደማይችል ይታወቃል። በስብሰባ የሚሉትን ይዞ ለህዝብ ከማድረስ አቋም መያዙ የሚያዋጣ ይሆናል። ንፁሃንን
እያፈናቀሉ ክልሉ ተፈናቃይ ከመቀበል ውጭ ሌላ ስራ እንዳይኖረው ሲያደርጉ ዝም ብሎ ማየት አክሳሪ ነው። ከዚህ በላይ ህዝብ በይፋ ሊዘመትበት አይችልም።

via getcahew shiferaw

እንኳን ለ127ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!ሀገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ሽህ አመታት ታሪኮች ባለቤት ናት። ከታሪኮቻችን ሁሉ ከፍ ብለው ከሚታዩት ውስጥ ደግሞ የአድዋ ድል አንዱ...
02/03/2023

እንኳን ለ127ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

ሀገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ሽህ አመታት ታሪኮች ባለቤት ናት። ከታሪኮቻችን ሁሉ ከፍ ብለው ከሚታዩት ውስጥ ደግሞ የአድዋ ድል አንዱ ነው። የአድዋ ድል ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጣሊያን ወረራ እራሷን ነፃ ለማውጣት የከቲት 23 ቀን1888 ዓ.ም አድዋ ላይ የጣሊያንን ጦር ገጥማ ድል ያደረገችበት ነው። የአድዋ ድል ታሪክ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በተውጣጡ ጀግኖች አባቶቻችን በንጉስ አፄ #ምኒልክና በንግስት እቴጌ #ጣይቱ ብርሃን ዘኢትዮጵያ የተመራ ሰራዊት በደምና አጥንት የተገኘ ደማቅ ታሪክ ነው። ይህ ታሪክ የኢትዮጵያውያን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የአለም የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ታሪክ ተደርጎ ይወሰዳል።

በንጉስ ምኒልክ የተመራው የአድዋ ድል የአለምን ታሪክ የቀየረ፣አዲስ አስተሳሰብን የወለደ፣የኢትዮጵያን ከፍታ በሚገባ ያሳየ ስለመሆኑ በርካታ ፀሀፍት በፁሁፎቻቸው አስፍረዋል። ያለ አፄ ምኒልክ መሪነት ድሉ አልተገኘም!!

ንጉስ አፄ #ምኒልክ በአድዋ የጣሊያንን ጦር ድል መንሳት አውሮፓውያን ለመላው ጥቁር ህዝቦች ያላቸውን የንቀት አስተሳሰብ ቅስም የሰበረና ከመሠረቱ የቀየረ ነው። "የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ክብር ማህተም፣ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው"።

ድሉ የመላው አለም ተፈጥሯዊ ክብር እና ሰብአዊ ክብር የታደሰበት ብቻ ሳይሆን የሰው ዘር ላይ ተደቅኖ የነበረው የህልውና ስጋት ጨለማው የተገፈፈበት እንዲሁም የነጭ የበላይነት መጥፎ አመለካከት የተወገደበት ታላቅ ድል ነው። ጣሊያኖች በአድዋ ድል ድባቅ ሲመቱ በሮም አደባባይ Viva Minilek Viva Tayitu እያሉ የኢትዮጵያን ጀግኖች ያወድሱ ነበር። በጋዜጦቻቸው ጭምር እያሳተሙ ለአለም ህዝብ የኢትዮጵያኖችን አይበገሬነት፣ ጀግንነትና ርህራሄ ይገልፁ ነበር።

የአድዋ ድል ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸውን ተጠቅመው ነፃነታቸውን ያስከበሩበት ብቻ ሳይሆን ሌሎች በቅኝ ግዛት ቀንበር ስር ሲማቅቁ የነበሩ አፍሪካዊያን ሀገራት ወገኖቻችንና ሌሎች ጥቁር ህዝቦች ለነፃነት ትግል እንዲነሳሱ ችቦ አብርተው ያሳዩበትም ነበር። የአድዋ ድል ሀገራችን ኢትዮጵያ በዲኘሎማሲው ዘርፍ ከፍተኛ ተቀባይነት እንዲኖራት ያስቻለ ድል ነው።

አስተዋይና ብልህ መሪ ያላት ሀገር ኢትዮጵያ ባልሰለጠነ ዘመን ህዝብን ከአራቱም ማዕዘን ቋንቋና እምነት ሳይገድበው ለነፃነቱ ለክብሩና ለሀገሩ ፍቅር "በአንድ እዝ ስር" እንዲሰባሰብ ማስቻል ምንኛ መታደል ነው? #ንጉስ ምኒልክና ንግስት እቴጌ #ጣይቱ ብርሃን- ዘኢትዮጵያ የሀገራቸውን ህዝብ አነቃንቀው ከ120ሽህ በላይ ተዋጊ ሃይል ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ሲያሰባስቡና በጠላት ላይ ድል ሲያደርጉ የመሪወቹን የመምራት ጥበብ(wisdom) አለማድነቅና አለመኩራት አይቻልም። በዚያ ዘመን የነበረን የሀገር ፍቅርና አንድነት ለዚህ ዘመን ትውልድ እንድንማርበት እድል የሚፈጥር ሆኖ እናገኘዋለን።

የአድዋ ድል ብዙ ጀግና ኢትዮጵያኖችን እንደነ አሉላ አባነጋ አይነቶቹን አፍሪካዊ ጀነራሎች፣አንደነ ፊታውሪሪ ገበየሁን፣እንደነ ባልቻ አባሳፎን፣እንደነ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዴነገዴ፣ የጉሙዝ ጀግኖችን፣የሱማሌ ጀግኖችን፣የጋምቤላ ጀግኖችን እንደነ ጀብደኛው ኦባላ ኒግዎ ፣የደቡብ ጀግኖችን፣የአፋር ጀግኖችን ወዘተ የፈጠረ ድል ነው። ሀገርን በደምና በአጥንት ያቆመና ያስከበረ ድል ነው። ሰለሆነም ሀገራችን ኢትዮጵያ ይህን የድል በዓል ብሄራዊ በዓል አድርጋ በየ አመቱ የካቲት 23 ቀን ታከብረዋለች። እያከበረችም ትቀጥላለች።

የአድዋ ድል ለእኛ ኢትዮጵያኖች አንድነትን፣ጀግንነትንና ፅናትን የምንላበስበት ይበልጥ የምናጠናክርበት፣ የሀገራችን ሰላም የምንጠብቅበት፣ ልማትና እድገት በሀገራችን እንዲረጋገጥ የምንተጋበት፣ መቻቻልና መከባበርን እውን የምናደርግበት ሊሆን ይገባል እንጅ በቁሞ ቀር ፖለቲካና የሀሠት ትርክት ተቸክሎ የወራሪውን ትህነግ የ27 አመት ቆይታ አይነት ለመቆየት መሻትና መፈለግ አያስፈልገንም።

የአማራ ህዝብ ከአድዋ ድል ሊወስደው የሚገባው ትልቅ ትምህርት አለ። የአባቶቹን ጀግንነት፣ጥበብ፣ ብልህነትና አስተዋይነት፣ እንዲሁም የአንድነትን መንፈስ ከእስራኤል ህዝቦች ሊማር ይገባዋል። እስሬኤሎች ካለመኖር ወደ መኖር ከሀገር አልባነት ወደ ሰለጠነና በቴክኖሎጅ በዳበር ኢኮኖሚ የተገነባ ሀገር የፈጠሩት የአንድነትን መንፈስ በመላበስና ወደ ተግባር በመቀየር ብቻ ነው። እኛ አማራወችም ከተደቀነብን ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ችግር መዳኛችን አንድነታችን በማጠናከር በድህነት ላይ ርብርብ በማድረግ በኢኮኖሚ የዳበረ ማህበረሰብ መገንባት ይጠበቅበታል። አንድነቱን ያጠናከረማህበረሰብ፣ በኢኮኖሚ የዳበረ ማህበረሰብ መገንባት ሁሌም የሚታፈርና የሚከበር ህዝብ ይሆናል። ስለሆነም በየደረጃው የሚገኝ ሁሉም የህብረተሠብ ክፍል ለመከበርና ለመታፈር ከፈለገ በተሠማራበት የስራ ዘርፍ ውጤት ማስመዝገብ ይገባዋል። ድሃ ሁሌም ተንበርካኪ እንጅ አንበርካኪ ሊሆን አይችልም። ክብሩንና የአባቶቹን የጀግንነት ተሪክ የሚፈልግ ሁሉ ድህነትን ታሪክ ማድረግ ይጠበቅበታል//ይጠበቅብናል።

በመጨረሻም የአማራ ህዝብ ከመቸውም ጊዜ በላይ አንድነቱን በማጠናከር በማንነቱ ምክንያት ለአሰቃቂ ሞትና ጭፍጨፋ፣ ስደትና መፈናቀል የሀብትና ንብረት ውድመት እያደረሱ አንሰው ሊያሳንሱት የሚፈልጉትን ጠባብ ሃይሎች በመመከት በሀገራችን ላይ የተጋረጠውን አደጋ ከሁሉም ሀገር ወዳድ ብሄር ብሄረሰብች ጋር በመሆን ሀገሩን ሊታደግ ይገባል። ምክንያቱም የአድዋ ድል ሀገርን ጠብቆ ያቆየ የአንድነት፣ የጀግንነትና የነፃነታችን ትልቁ ማህተማችን ነውና። እኛ ደግሞ የአባቶቻችን ልጆች የመሆን ታሪካዊ ሀላፊነት አለብንና።

#ክብር በዚያ ዘመን በሀገር ፍቅር ስሜት ሀገርን ከነጭ ወራሪ ለመታደግ በብልህ የአመራርነት ጥበብ መርተው አገር አስጠብቀው ለድልና ክብር ላበቁት እምየ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ!!
#ክብር ቋንቋና ዘር ሳይገድባቸው ከአራቱም ማዕዘን ተነስተው በጀግንነት ተዋግተው ጠላትን ድል ነስተው ሀገር አስከብረው ላሰከበሩን ጥንት አባቶቻችን!!

Address

Addis Ababa
1000

Telephone

+251912042760

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tamagne Hune ታማኝ ሁን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category