10/04/2023
ፐርፐዝብላክ ምን ምን ዘርፎች ላይ ተሰማርቷል ?
ኩባንያችን ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች በዓለም አቀፍ ደረጃ የጥቁሮችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለመገንባት በዋናነት በግብርና ፣ የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር ፣ በችርቻሮና በኢ-ኮሜርስ (በበይነ መረብ መገበያያ እና መሽጫ መድረክ) ላይ ትኩረቱን በማድረግ እየሠራ ይገኛል ፡፡
ግብርና ፡-
በ2026 እ.አ.አ 30 ሺ ሄክታር መሬትን ለማልማት እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አክሲዮን ማኅበር አሁን ላይ 2 ሺ 100 ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ የግብርና ምርቶችን በማልማት ላይ ይገኛል ፡፡
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እና በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በቆጂ ሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ በተቀናጀ የግብርና ልማት ላይ እየሠራ ሲሆን አትክልትና ፍራፍሬ (ሽንኩርት ፣ ቲማቲም ፣ ቃሪያ ፣ዝኩኒ ሀባብና ማንጎ ) እንዲሁም የፍየል ሥጋ ፣ የበሬ ሥጋ ፣ የእንስሳት መኖና ማር በስፋት ለማምረት በዕቅድ ተይዟል፡፡
የግብርና ምርት ማቀነባበር ፡-የፐርፐዝብላክ የአግሮፕሮሰሲንግ ከፍል በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ከተማ የተቀናጀ ባሕላዊ ምግቦች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ሥራ ያስጀመረ ሲሆን በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የኾነውን የሙዝ ቺፕስ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለመክፈት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፤ በጥቂት ጊዜ ውስጥም፣ የሙዝ ቺፕስ የድንች ቺፕስ እና ተያያዥ ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣ የቡና ፕሮሰሲንግ ፋብሪካ ( የተቆላ እና የተፈጨ የታሸገ ቡና) የሚያመርት ፋብሪካ፣ የኑድል ማምረቻ ፋብሪካ፣ የዱቄት ማምረቻ ፋብሪካ፣ የእንስሳት መኖ ማምረቻ ፋብሪካ፣ የእንስሳት(ከብቶች) ሥጋ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣ የፍሮዝን ቬጂቴብል ማምረቻ ፋብሪካ፣ የሞሪንጋ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣ የለውዝ ቅቤ ማምረቻ ፋብሪካ፣ የማር እና ሰም ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣ ኢንስታንት ኮፊ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ማሸጊያዎችን የሚያመርት ፋብሪካ፣ የወተት እና ተያያዥ ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣ ዓሣ እና የዓሣ ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን ለመክፈት ዕቅድ ይዟል፡፡
የችርቻሮ ሱቆች (Retail Stores):-
ከገበሬው በችርቻሮ መሸጫ መደብሮቻችን ጥራት ያላቸው የተቀናጁ የግብርና ውጤቶች ማለትም አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ቀጥታ ከገበሬው እንዲኹም ከአምራቾች በመረከብ በተመጣጣኝ ዋጋ ለኅብረተሰቡ እያደረሰ ይገኛል ፡፡
በኢትዮጵያ አሁን ላይ የችርቻሮ መሸጫ ሱቆች ያሉን ሲሆን በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች (በአትላስ ፣ ላፍቶ፣ ቡልቡላ ፣ ሰሚት ፣ አያትና አድዋ ድልድይ ) እንዲሁም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ወላይታ ሶዶ አትክልትና ፍራፍሬ ፣ የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶችን እንዲኹም ጥራት ያላቸው የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለኅብረተሰቡ እያከፋፈልን እንገኛለን ፡፡
ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት በመላ ሀገሪቱ 1 ሺ የችርቻሮ ሱቆችን በመክፈት ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የግብርና ውጤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ለሚገኘው የማኅበረሰብ ክፍል ለማቅረብ እየሠራ ይገኛል ፡፡
ኢ-ኮሜርስ
ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነውን የኢ-ኮሜርስ ዌብ ሳይት አበልፅጎ ሥራ ላይ በማዋል የግብይት ሥርዓቱን እያዘመነ ይገኛል፡፡ kegeberew.com የተሰኘውን የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ኢ-ኮሜርስ ሥርዓት ምርትና አገልግሎት አቅራቢዎች፣ አምራቾች እና ገዢዎች በአንድ ቦታ የሚገናኙበት እና የሚገበያዩበት ሲሆን የግብይት ሥርዓት ሕግጋትን እና ደንቦችን በማክበር በመዲናችን በሥራ ላይ ይገኛል፡፡
በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ደንበኞቻችን የሚፈልጉትን ምርትና አገልግሎት ኦንላይን ሆነው ሲያዙን በመረጡት ማድረሻ መንገድ ባሉበት ቦታ ለማድረስ የሚያስችል የሎጂስቲክ ሥርዓት ዘርግተን እርስዎን እየጠበቅን እንገኛለን ፡፡
ደንበኞቻችን በዌብ ሳይታችን፣ የስልክ ጥሪ በ 9858 ላይ በመደወል የሚፈልጉትን ምርት እንዲያገኙ ተመቻችቷል፡፡