11/09/2026
ከቤት ኪራይ ያውጣን!
(የአመት በዓል ትውስታ...☺️)
ልጅ ሆነን ለአዲስ ዓመት በየቤቱ እየዞርን “እንቁጣጣሽ!” ስንል፣
“በየዓመቱ ያምጣሽ!”፣
“ስትዳር ኩታ!” የሚሉ መልሶች ባደግኩበት አካባቢ የተለመዱ ነበሩ። (ከስጦታና ጉርሻው በተጨማሪ ማለቴ ነው።😁)
ባቀረቡን ልክ የመውደዳቸውን መጠን በድምፃቸው ዜማና በመሳማቸው ያሳዩን ነበር። (ልጅነት ግን እንዴት ደስ ይላል? ☺️)
የወንድ አያቴ ግን ከሌሎቹ ለየት ይል ነበር።
“ባባ እንቁጣጣሽ!” ስንለው፣
“ከቤት ኪራይ ያውጣሽ!”
“ከቤት ኪራይ ያውጣህ!” ነበር የሚመልስልን።
ግራ ይገባኝ ነበር። ልጅ ስለነበርኩም ብዙም አላስተነተንኩትም። (ከሞተ አሁን 16 ዓመት ሆኖታል። አላህ ይዘንለት! 😪)
ዛሬ ጠዋት እናቴን በስልክ “እንቁጣጣሽ!” ስላት፣ ልክ እንደ አያቴ፣ “ከቤት ኪራይ ያውጣህ!” አለችኝና በትዝታ ወደ ኋላ መለሰችኝ።
የአያቴ የዓመት በዓል ምኞት ትርጉም ተገለጠልኝ። ልጅ ሆኜ ያልገባኝን ነገር፣ ዛሬ ግን በደንብ አስተንትኜ ተረዳሁት።
“ከቤት ኪራይ ያውጣህ” ማለት በእውነቱ ትልቅ ምርቃት ነው። ያኔ እንዲያ ሲመርቀን፣ ከኪራይ ውጣ ውረድ ነፃ የሆነ ሕይወት እየተመኘልን ነበር ለካ።
አሁን ላይ በሥራዬ የማገኛቸው ሰዎችም ተመሳሳይ ምኞት አላቸው፤ የተረጋጋ፣ ሰላም ያለው፣ ልባቸው የሚያርፍበት፣ የኔ የሚሉትን የራሳቸው የሆነ ቤት ማግኘት።
ስለዚህ ሪል እስቴት ሥራ ለእኔ ጣራና ግድግዳ መሸጥ ብቻ አይደለም። የሰዎችን የዓመታት ምኞት እውን ለማድረግ ከጎናቸው በመሆን አብሮ የመጓዝ ሂደት እና ትክክለኛ ምርጫ እንዲመርጡ ማማከር እንጂ።
እና በዚህ አዲስ ዓመት ለራሳችን ከምንመኛቸው ነገሮች አንዱ፣ የግላችን ቤት መግዛት ይሁን።
“ከቤት ኪራይ ያውጣችሁ!”
ይህ የአያቴ ምርቃት ነበር።
ዛሬ ደግሞ ለእናንተ የእኔ የአዲስ ዓመት ምኞት ነው። አማካሪ የፈለጋችሁ 'ለት ደግሞ እኔ አለሁ።
መልካም አዲስ ዓመት!
Ahmedin