23/12/2023
ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ማነው?
አላማውስ ምንድነው?
ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን በቤት ልማት ፣ በተዘዋዋሪ የቁጠባ ፈንድ ፣ በአይቲ እና ማርኬቲንግ መስኮች በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ የካበተ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተቋቋመ አገር በቀል ኩባንያ ነው፡፡
ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን የከተማችንን ብሎም የአገራችንን የመኖሪያ ቤት አቅርቦት እጥረት እንዲሁም በአብዛኛው ማህበረሰብ ዘንድ የመግዛት አቅም ውስንነት ላይ መጠነ ሰፊ ጥናት በማድረግ የችግሮቹን መንስኤዎች በመለየት እና የመፍትሔ ሀሳቦችን በመቀመር ተዘዋዋሪ የቁጠባ ፈንድ ላይ የተመሰረተ “Key-CHF” የተሰኘ ሞዴል ቀርፆ በቀጣይ 10 አመታት ውስጥ ለ 100,000 ቤት ፈላጊዎች በሞዴሉ መሰረት በአዲስ አበባ እና በክልል ዋና ዋና ከተሞች ላይ ግንባታቸው በወጪ ቀናሽ የግንባታ ቴክኖሎጂዎች የተጠናቀቁ ቤቶችን ከአልሚዎች ጋር በተደረገ ስምምነት መሰረት በመግዛት በአመት ሁለት ጊዜ እድለኞችን በዕጣ በመለየት የቤት ባለቤት ለማድረግ እየሰራ ያለ ድርጅት ነው፡፡
የመኖሪያ ቤት ችግር መንስኤዎች
በአገራችን ለአመታት የቆየ እና እየተባባሰ የመጣው የመኖሪያ ቤት ችግር ማህበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መንስኤዎች ያሉት ሲሆን ዋናዎቹ ከዚህ ቀጥሎ ተዘርዝሯል፡፡
እጅግ የተጋነነ የመኖሪያ ቤት መሸጫ ዋጋ!
የመሬት እና የግንባታ ግብአቶች ዋጋ ንረት!
ማህበረሰብ ተኮር ፕሮጀክቶች በሚፈለገው ልክ መቀጠል አለመቻላቸው!
ዘርፉ ላልተገባ ትርፍ ፈላጊዎች የተጋለጠ መሆኑ!
መሬትን በአግባቡ የመጠቀም ልማድ አለመኖር!
የዘመነ እና ወጪ ቀናሽ የግንባታ ቴክኖሎጂን አለመጠቀም! ወ.ዘ.ተ
በመሆኑም ያሉንን ማህበራዊ እሴቶች እና ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማካተት በትብብር የምንሰራበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡
በዚሁ መሰረት ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ተዘዋዋሪ የቁጠባ ፈንድ ላይ የተመሰረተ ቤት ፈላጊዎችን የቤት ባለቤት የሚያደርግ “Key-CHF” የተሰኘ ሞዴል ቀርፆ ወደ ተግባር ገብቷል፡፡
1. Key-CHF ሞዴል
“Key-CHF” (Key Common Housing Fund) ሞዴል ከ አነስተኛ እስከ መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በአነስተኛ የካፒታል እና የአገልግሎት ክፍያ እንዲሁም ለ 30 ዓመታት በሚቆይ መጠነኛ ወርሀዊ ቁጠባ በጠቅላላው ከወቅቱ የቤት ዋጋ ግምት አንፃር እስከ 65 % ድረስ ብቻ በሚያደርጉት የገንዘብ አስተዋፅዎ በዓመት ሁለት ጊዜ እድለኞችን በእጣ በመለየት በ 10 ዓመታት ውስጥ 100,000 ቤት ፈላጊዎችን የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
በምሳሌ ለማስረዳት
የመጀመሪያ እጣ ላይ ባለ አንድ መኝታ ቤት እድለኛ የሆነ ቤት ፈላጊ የሚጠበቅበት ክፍያ፡-
• የካፒታል እና የአገልግሎት ክፍያ (ሲመዘገብ) = 77,280
• የአምስት አመት የኢንሹራንስ ክፍያ (ሲመዘገብ) = 2,672
• ወርሃዊ ቁጠባ የአገልግሎት ክፍያን አካቶ = 2,230
• እጣ ሲወጣ የሚፈፀም ክፍያ = 300,000
• ዕጣ የወጣበት ቤት ለ አምስት አመት ገቢ እንዲፈጥር ዕጣ የደረሰው ግለሰብ በወቅቱ የኪራይ ዋጋ ወርሀዊ መዋጮ በማከል እየከፈለ እንዲኖርበት ቅድሚያ ይሰጠዋል፤ይህ ካልሆነ ሊያከራየው ወይም ኪ በአደራ እንዲያከራይለት ማድረግ ይችላል፡፡
• ቤቱ ለ 5 ዓመት ተጨማሪ ገቢ ካስገኘ በኋላ የሚፈፀም ክፍያ = 300,000
• ወርሀዊ ቁጠባ ለቀሪ 25 ዓመታት እጥፍ ሆኖ ይቀጥላል = 4,230
የካፒታል ክፍያ እና ወርሀዊ ቁጠባ አጋራችን በሆነው ዳሽን ባንክ በተከፈተው ዝግ የሒሳብ ቁጥር (1234) የሚፈፀም ሲሆን የአገልግሎት ክፍያ በተከፈተው ተንቀሳቃሽ የሒሳብ ቁጥር (1235) ይፈፀማል፡፡ በተጨማሪ ሁሉም ክፍያዎች በቡና ኢንሹራንስ ሙሉ የአፃፀም ዋስትና የተገባላቸው ናቸው፡፡
የሞዴሉ አስፈፃሚዎች
ኪ ሀውሲንግ ሶሎሽን
• ብሉዞን ማርኬቲንግ ኩባንያ
• ትረስት-ቴክ አይቲ ሶሉሽን
• አቢጃታ ሻላ ትሬዲንግ
አጋር እና ተባባሪ ተቋማት
• መንግስታዊ ተቋማት
• ዳሽን ባንክ አ.ማ
• ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ
• አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
• ሪልእስቴት አልሚዎች ይገኙበታል፡፡
ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
https://t.me/+feU2rB6LGgYzNDFk
0913808984
0909841028
ጥቂት ቀናት ቀርተዋል ይህንን የአንድ ጊዜ እድል እንዳያመልጥዎ ይደውሉልን !