Beza Homes

Beza Homes ቅንጡ አፓርትመንት እና የንግድ ሱቆችን በተመጣጣኝ ዋጋ እኛ ጋ ያገኛሉ
0954258617

16/09/2026

Enyi Real Estate 🏡

👉ቦሌ ቡልቡላ compund
👉2B+G10+T
👉 2ሊፍት
👉ከ 2ተኛ ጀምሮ መኖሪያ
👉በ2 አመት የሚረከብ
👉ከ 10.8 ሚሊዬን ብር ሙሉ ክፍያ ጀምሮ

16/09/2026

0954258617 ይደውሉ

16/09/2026

በቦሌ 24 ዲጅታል ካርታ ያላቸው ጥንቅቅ ብለው ያለቁ አፓርትመንቶች በ 50% ቅድመ ክፍያ ለሽያጭ አቅርበናል
ለበለጠ መረጃ 0954258617

ቤት ስትገዙ “አጣራ” ይባላል። ግን ምን እንደምታጣሩ ታውቃላችሁ?ቤት መግዛት ብር መክፈል ብቻ አይደለም።ሰነዶቹን ማረጋገጥ እና የምትገዙትን ንብረት በትክክል ማጣራት ነው።በቤታችሁ ሆናችሁ ለ...
14/09/2026

ቤት ስትገዙ “አጣራ” ይባላል። ግን ምን እንደምታጣሩ ታውቃላችሁ?

ቤት መግዛት ብር መክፈል ብቻ አይደለም።
ሰነዶቹን ማረጋገጥ እና የምትገዙትን ንብረት በትክክል ማጣራት ነው።

በቤታችሁ ሆናችሁ ለመጀመር እነዚህን 3 ነገሮች ተመልከቱ።

1️⃣ የንግድ ፈቃድ

በዚህ ላይ 3 ነገሮችን አረጋግጡ፦

• ስም — በንግድ ፈቃዱ ላይ ያለው ስም ከካርታው ላይ ካለው ስም ጋር ይመሳሰላል?
• የስራ ዘርፍ — የሪል እስቴት ልማት/ማካፈል የሚመለከተው የስራ ዘርፍ በፈቃዱ ላይ አለ?
• የታደሰ ፈቃድ — ፈቃዱ በወቅቱ የታደሰ መሆኑን አረጋግጡ።

2️⃣ ካርታ

ካርታውን በቀላሉ አትዩት። አረጋግጡት።

• የመጀመሪያው/ዲጂታል ካርታ መሆኑን
• የካርታ ቁጥሩ በAgreement ላይ ካለው ቁጥር ጋር መመሳሰሉን
• በካርታው ላይ ያለው ስም ከንግድ ፈቃዱ ጋር መመሳሰሉን

በተጨማሪም እነዚህን መረጃዎች ይመዝግቡ፦

📌 የሊዝ ዘመን
📌 የይዞታ ስፋት
📌 X-Y Coordinates
📌 Serial Number

እነዚህ ለተጨማሪ ምርመራ በጣም ይጠቅማሉ።

3️⃣ Agreement

Agreement ላይ ያለውን ብቻ አትፈርሙ። ያለብዎትንም ያንብቡ።

በተለይ Hidden Fees ካሉ ይመልከቱ፦

1. 💰 ተጨማሪ የሊዝ ክፍያ አለ?
2. ⚡ Generator / Transformer ወይም ተመሳሳይ ክፍያዎች አሉ?
3. 📈 የግንባታ ዕቃ ዋጋ ሲጨምር የእናንተም ክፍያ እንዲጨምር የሚያደርግ Inflation/Escalation Clause አለ?

⚠️ አስታውሱ

እነዚህ 3 ነገሮች ለመጀመሪያ ማጣሪያ ይረዱዎታል። ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ንብረት ከመግዛታችሁ በፊት ግን ብቃት ካለው የህግ ባለሙያ እና ከሚመለከታቸው ሙሉ ማረጋገጫ ያግኙ።

አንድ ሰነድ ሳታጣሩ ብር አትክፈሉ።

📌 ይህን Post SAVE አድርጉት — ቤት ለመግዛት ሲያስቡ ያስፈልጋችኋል።
📲 ለሌላ ቤት ገዢ SHARE አድርጉት።

ለቤት እና ሪል እስቴት መረጃ Follow ያድርጉን።

#ቤትግዢ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ቤት ገዝተው ካርታ ለማዞር ወደ ክፍለ ከተማ ሲሄዱ...ይህ ወጪ ከፊትዎ ይጠብቅዎታል!ስንት እንደሆነ ያውቃሉ?ብዙ ገዢዎች የቤት ግዢ ውል ተዋውለው የመጨረሻውን የካርታ ስም ዝውውር ለማከናወን ...
10/09/2026

ቤት ገዝተው ካርታ ለማዞር ወደ ክፍለ ከተማ ሲሄዱ...ይህ ወጪ ከፊትዎ ይጠብቅዎታል!
ስንት እንደሆነ ያውቃሉ?

ብዙ ገዢዎች የቤት ግዢ ውል ተዋውለው የመጨረሻውን የካርታ ስም ዝውውር ለማከናወን ወደ መሬት አስተዳደር ቢሮ ሲያመሩ፣ ቀድመው ካልተዘጋጁ ወጪዉ ያቀዱትን የገንዘብ በጀት ሊያናጋው ይችላል። የመንግስትን የስም ማዛወሪያ (አሹራ)እና ተጨማሪ ክፍያዎች ገና ከጀማሪው ከግምት ውስጥ አለማስገባት ደግሞ ትልቅ የፋይናንስ ኪሳራ እና የእንቅስቃሴ መስተጓጎል ውስጥ ይከትታል።

በአዲስ አበባ ከተማ ማንኛውም ገዢ ቤት እንደገዛ ወዲያውኑ 6.5% የመንግስት ስም ማዛወሪያ ክፍያ መክፈል ይኖርበታል። ነገር ግን አብዛኛው ሰው እንደሚስበው ይህ 6.5% የሚሰላው በውሉ ላይ በተጻፈው የቤት መግዣ ዋጋ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ክፍለ ከተማው በካሬ ሜትር ባስቀመጠው ህጋዊ ዝቅተኛ የቦታ ተመን እና በእናንተ የውል ዋጋ መካከል ከፍ ባለው ላይ ተመስርቶ ነው። ይህ ክፍያ በውስጡ 4% የአሹራ ወይም የስም ዝውውር፣ 2% የቴምብር ቀረጥ እና 0.5% የአደጋ ጊዜና የዋስትና ፈንድ ክፍያዎችን ይይዛል።

ይህንን ወደ ተጨባጭ ምሳሌ ስንለውጠው፣ በ 10 ሚሊዮን ብር ቤት የገዛ ሰው የካርታ ስም ለማዞር ብቻ ተጨማሪ 650,000 ብር የመንግስት ክፍያ በእጁ ላይ ሊኖረው ይገባል። ስለዚህ ማንኛውንም የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ሲያቅዱ በሻጩ ዋጋ ላይ ብቻ ሳይመሰረቱ፣ የመጨረሻዎቹን የዝውውር ወጪዎች ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ አብረው ማሰላሰል ብልህነት ነው።

ለመሆኑ በእርስዎ እይታ በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ገበያ ይህ የመንግስት 6.5% (አሹራ) ክፍያ ለአሁኑ ገበያ ተገቢ ነው ወይስ ለቤት ባለቤትነት እንቅፋት እየሆነ ነው? ሀሳብዎን በኮመንት ላይ ያስቀምጡልኝ።
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስም Share Repost ያድርጉ!!

09/09/2026

100% ጥንቅቅ ብለው ያለቁ አፓርትመንቶች በመሀል 24
በ 50% ቅድመ ክፍል ለበለጠ መረጃ በ 0954258617 ይደውሉ

10 የገንዘብ ቃላት ሁሉም ሰው ማወቅ ያለበት ጉዳይ!ስኬታማ ሰዎች በየቀኑ የሚጠቀሙባቸው 10 ወሳኝ የገንዘብ ቃላት! እነዚህን ፅንሰ ሀሳቦች በመረዳት የገንዘብ ውሳኔዎችን በከፍተኛ ደረጃ መቀ...
09/09/2026

10 የገንዘብ ቃላት ሁሉም ሰው ማወቅ ያለበት ጉዳይ!
ስኬታማ ሰዎች በየቀኑ የሚጠቀሙባቸው 10 ወሳኝ የገንዘብ ቃላት!
እነዚህን ፅንሰ ሀሳቦች በመረዳት የገንዘብ ውሳኔዎችን በከፍተኛ ደረጃ መቀየር ይቻላል።
1. የዋጋ ግሽበት (Inflation)
በጊዜ ሂደት የእቃዎችና የአገልግሎቶች ዋጋ መጨመር የገንዘብን የመግዛት አቅም ይቀንሳል። ዛሬ በ100 ብር የሚገዛ ነገር በሚቀጥለው ዓመት 130 ብር ቢሆን 100 ብሩ በቁጥር አልቀነሰም የመግዛት አቅሙ ግን ቀንሷል።
2. የገንዘብ የመግዛት አቅም (Purchasing Power)
ዋናው ነገር በእጅ ያለው የገንዘብ መጠን ሳይሆን በዚያ ገንዘብ ምን ያህል ነገር መግዛት እንደሚቻል ነው።
በተግባር የሚገኘው ገቢ በየዓመቱ ቢጨምርም የእቃዎች ዋጋ ከገቢው በበለጠ ፍጥነት ከጨመረ በእውነቱ የመግዛት አቅም እየቀነሰ ነው ማለት ነዉ።
3. የአስቸኳይ ጊዜ ቁጠባ (Emergency Fund)
ለማይጠበቁ አስቸኳይ ችግሮች ብቻ የሚቀመጥ ገንዘብ ነው። ለጉዞ ወይም ለግዢ አይደለም። ስራ ቢታጣ፣ ስልክ ቢበላሽ ወይም ድንገተኛ የህክምና ወጪ ቢመጣ? ቢያንስ የ3 እስከ 6 ወር የኑሮ ወጪን የሚሸፍን ገንዘብ በተለየ የቁጠባ ሂሳብ ማስቀመጥ ይመከራል።
4. ፈጣን የገንዘብ መቀየሪያ አቅም (Liquidity)
አንድን ንብረት በፍጥነት ወደ ጥሬ ገንዘብ የመቀየር አቅም ነው።ጥሬ ገንዘብ ወዲያውኑ መጠቀም ይቻላል። ወርቅ በፍጥነት ይሸጣል። ንብረት/ቤት ግን ለመሸጥ ጊዜ ይወስዳል። ስለዚህ ሰዎች በእጃቸው ቶሎ ወደ ገንዘብ የሚቀየር ነገር ሊኖራቸው ይገባል።
5. ገንዘብን ማሰራጨት (Diversification)
ገንዘብን በአንድ ቦታ ብቻ አለማስቀመጥ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ማሰራጨት።
ሁሉንም ቁጠባ በአንድ ቦታ ከማስቀመጥ ይልቅ በአክሲዮን፣ በሪል እስቴት እና ሌሎች ቢዝነሶች ላይ ማሰራጨት አንዱ ቢወድቅ ሌሎቹ ይደግፋሉ። በዛ ገንዘባችንን ማዳን እንችላለን።
6. የአማራጭ ዋጋ (Opportunity Cost)
አንድን የገንዘብ ውሳኔ ሲመረጥ በምትኩ ሌላ አማራጭ ላይ የሚጣው ዕድል ወይም ጥቅም ነው።
ገንዘብን ለላፕቶፕ ሲወጣ ያ ገንዘብ በኢንቨስትመንት(በዛ ገንዘብ ሌላ ነገር መግዛት) ሊያመጣ የሚችለውን ትርፍ አቅም ማለት ነው።
7. ወለድ እድገት (Compounding)
ገንዘብ ትርፍ ያመጣል ያገኘው ትርፍ ራሱ ደግሞ ተጨማሪ ትርፍ ያመጣል። በቀላሉ ገንዘብ ገንዘብ ይወልዳል።
ቀድሞ ኢንቨስት ማድረግ ሲጀመር ገንዘብ ለመደጋገምና ለማደግ የበለጠ ጊዜ ያገኛል።
8. የጠቅላላ ሀብት መጠን (Net Worth)
ያለ ንብረት ሁሉ ሲቀነስ ያለ ዕዳ = የጠቅላላ ሀብት መጠን (Net Worth) ይባላል።
ንብረት 100,000 ብር ሆኖ ዕዳ 40,000 ብር ቢሆን Net Worth 60,000 ብር ነው።
9. የገንዘብ ነፃነት (Financial Freedom)
ኑሮን ለመሸፈን በደመወዝ ላይ ብቻ ሳይመሰረቱ በቂ ንብረትና ገቢ የሚያመነጩ ኢንቨስትመንቶች ሲኖሩ የሚገኝ ነፃነት ነው።
ኢንቨስትመንቶች የኑሮ ወጪን ሙሉ በሙሉ ሲሸፍኑ ለኑሮ በየወሩ በደመወዝ ስራ ላይ ብቻ መደገፍ ያቆማሉ።
10. የኪሳራ ፍርሃት
ሰዎች ትርፍ ለማግኘት ከመጣጣር ይልቅ የደረሰባቸውን ኪሳራ ለማስቀረት ወይም ላለመቀበል የሚወስዱት ስሜታዊ ውሳኔ ነው።
የወደቀን ኢንቨስትመንት ወይም እየከሰረ ያለን ንግድ ኪሳራዬን አልቀበልም ብሎ በግድ ይዞ መቀጠል ይበልጥ ትልቅ ኪሳራ ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋል።
5,000 ብር ማጣት የሚያስከትለው ስሜታዊ ህመም 5,000 ብር በድንገት ከማግኘት ከሚገኝ ደስታ በላይ በአእምሯችን ውስጥ ጎልቶ ይታያል።

ከእነዚህ ቃላት ውስጥ ዛሬ አዲስ የሆነባችሁ የትኛው ነው?
በኮሜንት ንገሩኝ።
ለወደፊት እንድታገኙት Save አድርጉት ለጓደኞቻችሁ Share አድርጉ።

እነዚህን የገንዘብ ህጎች ካየን ትልቁ ጥያቄ ገንዘብዎ በግሽበት የመግዛት አቅሙ እንዲቀንስ ይፈቅዳሉ? ወይስ አስተማማኝ ንብረት ላይ በማዋል ሀብትዎን ይገነባሉ?

የወደፊት መኖሪያዎንና ኢንቨስትመንትዎን ያለስጋት ከ ቴምር ፕሮፐርቲስ(Temer Properties) ጋር ያረጋግጡ!

አፓርትመንቶች
📍 ⚡️መገናኛ ⚡️ሳርቤት ⚡️ቡልጋርያ⚡️አዋሬ⚡️አያት
ከ20% ቅድመ ክፋያ ጀምሮ
እስከ የ35% የሚደርስ ቅናሸ አዘጋጅተን እንጠብቆታለን።

🛒የንግድ ሱቆች
📍 ⚡️ሳርቤት ⚡️ፒያሳ ⚡️ቡልጋርያ ⚡️ገላን/ቃሊቲ ከሮቢካ ሆቴል ፊትለፊት
ከ2 ሚሊዮን ብር አጠቃላይ ክፋያ ወይም 900ሺ ብር ቅድመ ክፋያ ጀምሮ አቅርበናል።

ከሀገር ዉጪ ላላችሁ ባላችሁበት ሆናችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ለበለጠ መረጃ
በ 0954258617 ይደውሉ

7 ሚሊዮን ብር ቤት በባንክ ብድር ሲገዛ በመጨረሻ ስንት ብር እንደሚከፉሉ ያቃሉ?ብዙ ሰዎች ቤት ሲገዙ የሚያዩት የቤቱ ዋጋ 7 ሚሊዮን ብር ነው የሚለውን ቁጥር ብቻ ነው። ነገር ግን 25% ቅ...
05/09/2026

7 ሚሊዮን ብር ቤት በባንክ ብድር ሲገዛ በመጨረሻ ስንት ብር እንደሚከፉሉ ያቃሉ?

ብዙ ሰዎች ቤት ሲገዙ የሚያዩት የቤቱ ዋጋ 7 ሚሊዮን ብር ነው የሚለውን ቁጥር ብቻ ነው። ነገር ግን 25% ቅድመ ክፍያ በትንሹ ያስፈልጋል። ቀሪውን 75% በባንክ ብድር ሲሸፍኑ የሚከፍሉት የፋይናንስ ስሌት ይህ ነው።
እስቲ በቀላል ምሳሌ እንየው
የቤቱ አጠቃላይ ዋጋ 7,000,000 ብር
የቅድመ ክፍያ (25%) 1,750,000 ብር (ከእጅዎ የሚከፈል)
የተበደሩት/የባንክ ብድር መጠን (75%) 5,250,000 ብር
የባንክ ወለድ 21%
የክፍያ ጊዜ 15 ዓመት (180 ወራት)
በዚህ ምሳሌ የሚጠቀምበት የብድር አሰራር በየወሩ እኩል ክፍያ የሚከፈልበት ይሆናል።
በየወሩ ስንት ይከፍላል?
5.25 ሚሊዮን ብርን በ 21% ዓመታዊ ኢንተረስት ለ 15 ዓመት ብትበደር በየወሩ ወደ 96,107 ብር ያህል መክፈል ይኖርበታል።
ይህም ማለት በዓመት በግምት 1.15 ሚሊዮን ብር ያህል ለባንኩ ይከፈላል ማለት ነው።
15 ዓመቱ ሲያልቅ ለባንኩ ምን ያህል ይከፍላል?
96,107 ብር × 180 ወራት
= 17,299,286 ብር ያህል ይሆናል
ስለዚህ 5.25 ሚሊዮን ብር የተበደርከውን ገንዘብ በ 15 ዓመት ስትጨርስ ለባንኩ ብቻ በድምሩ ወደ 17.30 ሚሊዮን ብር ይከፈላል።
ከዚህ ውስጥ
የተበደረው ዋና ገንዘብ = 5,250,000 ብር
ለባንክ የሚከፈለው ኢንተረስት ≈ 12,049,286 ብር
ጠቅላላ ለቤቱ የሚወጣው ወጪ (ቅድመ ክፍያን ጨምሮ)
የመጀመሪያ 25% ቅድመ ክፍያ 1,750,000 ብር
ለባንክ የተከፈለ ጠቅላላ ክፍያ 17,299,286 ብር
የቤቱ አጠቃላይ ወጪ = 19,049,286 ብር ይሆናል።
ይህ ምን ያሳያል?
በቀላሉ ስንመለከተው 7 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለውን ቤት 25% (1.75 ሚሊዮን ብር) ቅድመ ክፍያ ከፍለው ቀሪውን በ 21% ኢንተረስት ለ 15 ዓመት በባንክ ብድር ሲገዙ የቤቱ አጠቃላይ ወጪ 7 ሚሊዮን ሳይሆን ወደ 19.05 ሚሊዮን ብር ይደርሳል።
ማለትም ከተበደሩት 5.25 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ 12.05 ሚሊዮን ብር ያህል በኢንተረስት ብቻ ይከፈላል።

ይህ ምሳሌ 21% ዓመታዊ ኢንተረስት 180 ወር እኩል የወር ክፍያ በሚል ስሌት የተሰራ ነው።
ከዚህ ምን እንማራለን?
ቤት ለመግዛት የቤቱን ዋጋ ብቻ ማየት በቂ አይደለም።
ከመግዛትህ በፊት እነዚህን 4 ነገሮች ሁልጊዜ አስላ
1. የመጀመሪያ ክፍያ
2. የወር ክፍያ
3. ጠቅላላ ወለድ ወጪ
4. በመጨረሻ ለቤቱ የምትከፍለው ጠቅላላ ገንዘብ
እንዲሁም የቤቱ ዋጋ በጊዜ ሂደት ሊጨምር ይችላል ስለዚህ በኢንተረስት ምን ያህል ከፈልኩ? ብቻ ሳይሆን ይህ ቤት በ 15 ዓመት ውስጥ ምን ያህል ዋጋ ሊኖረው ይችላል? የሚለውንም ማሰብ ያስፈልጋል።
ቤት መግዛት የሚጀምረው በ ስንት ነው? አይደለም በመጨረሻ ስንት ነው የምከፍለው? ነው።

እርሶስ በባንክ ብድር ቤት መግዛትን እንደ ጥሩ የፋይናንስ አማራጭ ያዩታል ወይስ የወለድ አሰራሩ ያሰጋዎታል? ሀሳብዎን በኮመንት ያጋሩ።

በየወሩ ለባንክ ከፍተኛ ወለድ ከመክፈል ይልቅ ያለምንም ወለድ በከፈልከው ልክ የእጅህን ዋጋ የምታገኝበትን ቴምር ፕሮፐርቲስ አማራጮችን አቅርቦል።

የወደፊት መኖሪያዎንና ኢንቨስትመንትዎን ያለስጋት ከ ቴምር ፕሮፐርቲስ(Temer Properties) ጋር ያረጋግጡ!

አፓርትመንቶች
📍 ⚡️መገናኛ ⚡️ሳርቤት ⚡️ቡልጋርያ⚡️አዋሬ⚡️አያት
ከ20% ቅድመ ክፋያ ጀምሮ
እስከ የ35% የሚደርስ ቅናሸ አዘጋጅተን እንጠብቆታለን።

🛒የንግድ ሱቆች
📍 ⚡️ሳርቤት ⚡️ፒያሳ ⚡️ቡልጋርያ ⚡️ገላን/ቃሊቲ ከሮቢካ ሆቴል ፊትለፊት
ከ2 ሚሊዮን ብር አጠቃላይ ክፋያ ወይም 900ሺ ብር ቅድመ ክፋያ ጀምሮ አቅርበናል።

ከሀገር ዉጪ ላላችሁ ባላችሁበት ሆናችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ለበለጠ መረጃ
☎️0954258617ይደውሉ!!

በየቀኑ ብዙ ገዢዎች በስሜት እና በቂ መረጃ ባለመያዝ በሚወስኑት ውሳኔ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ያጣሉ።አብዛኞቹ የቤት አሻሻጮች (ኤጀንቶች) የማይነግሩዋችሁ 5 አሰቃቂ የሪል እስቴት ...
05/09/2026

በየቀኑ ብዙ ገዢዎች በስሜት እና በቂ መረጃ ባለመያዝ በሚወስኑት ውሳኔ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ያጣሉ።
አብዛኞቹ የቤት አሻሻጮች (ኤጀንቶች) የማይነግሩዋችሁ 5 አሰቃቂ የሪል እስቴት እውነታዎች
በየቀኑ ብዙ ገዢዎች በስሜት እና በቂ መረጃ ባለመያዝ በሚወስኑት ውሳኔ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ያጣሉ።

የመጀመሪያ ቤትዎን እየገዙ ከሆነ፣ አፓርትመንት ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ካሰቡ ወይም የንብረት ሀብትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ—የሪል እስቴት ገበያ ድብቅ የፋይናንስ ወጥመዶች የበዙበት ነው። ዋናው ችግር አብዛኛው ገዢ ትምህርቱን የሚማረው በከባድ ድካም ያገኘው ገንዘብ ከባንክ አካውንቱ ወጥቶ ከተጠናቀቀ በኋላ መሆኑ ነው።

ሀብትዎን ለመጠበቅ እና ስጋቱ የተጠና የንብረት ግዢ ለመፈጸም፣ በሚቀጥለው የሽያጭ ውልዎ ላይ ከመፈረምዎ በፊት ሊተገብሯቸው የሚገቡ 5 ወርቃማ ህጎች እነዚህ ናቸው፦

1. ከአትራፊዎች መግዛት ያቁሙ—ብር አስቸኳይ ከፈለጉ ሰዎች ፈልጋችሁ ግዙ
ከአትራፊዎች ወይም ከፍተኛ ትርፍ ከሚፈልጉ ሰዎች ጋር ለመደራደር ስትሞክሩ፣ ሻጩ ሙሉ ብልጫ ባለውበት የድርድር ሜዳ ውስጥ ነው የምትገቡት።

እውነተኛ እሴት ለማግኘት፣ ገንዘብዎን በተለያዩ ምክንያቶች አስቸኳይ ብር ወደሚፈልጉ ሻጮች አቅጣጫ አድርጉ፦
* በውርስ ክፍፍል ምክንያት የሚሸጡ ንብረቶች
* ወደ ውጭ ሀገር ለመውጣት ፈጣን ገንዘብ የሚፈልጉ ሻጮች
* በፍቺ ወይም በህጋዊ ምክንያቶች የሀብት ክፍፍል የሚያደርጉ
> የስትራቴጂ የበላይነት፦ የሰውን ችግር እየተጠቀማችሁበት አይደለም—እነሱ በጣም በሚፈልጉበት ሰዓት ወሳኝ የሆነ ፈጣን ገንዘብ እያቀረባችሁላቸው ነው። ይህም እነሱ ፈጣን ብር የሚያገኙበት፣ እናንተ ደግሞ ከገበያ ዋጋ በታች የሚያገኙበት እውነተኛ ሁለታችሁም ተጠቃሚ የምትሆኑበት (Win-Win) ሁኔታን ይፈጥራል።

2. ሙሉ ብር የመክፈል አቅም ካላችሁ፣ ያላለቀ (ኦፍ-ፕላን) ቤት አትገዙ
ያላለቁ አፓርትመንቶች በማስተዋወቂያ ወረቀቶች ላይ፣ በ3D ዲዛይኖች እና በወደፊት የዋጋ ጭማሪ ቃልኪዳናቸው በጣም ማራኪ ይመስላሉ። ነገር ግን በእጃችሁ ሙሉ cash ካለ፣ የአልሚዎችን የግንባታ ስጋት (risk) መሸከም ትልቅ የስትራቴጂ ስህተት ነው።

* ያላለቁ ፕሮጀክቶች ለግንባታ መዘግየት፣ ለአልሚዎች ከስራ ውጪ መሆን እና ለዕቃዎች ዋጋ ጭማሪ ያጋልጡዎታል።
* በእጅ የሚጨበጥ ንብረት ወዲያውኑ መረከብ እየቻሉ ለምን በሰነድ ላይ ባሉ ቃልኪዳኖች ላይ ይወራረዳሉ?
በዘርፉ እንደሚባለው፦ «ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን ይሻላል»። አቅሙ ካላችሁ ያላለቀ ቤት ገዝታችሁ ከሌላው ጋር ከመጋፋት ይልቅ ሙሉ በሙሉ ያለቀና ለመረከብ ዝግጁ የሆነ ንብረት ግዙ።

3. «ርካሽ ነው» ብላችሁ ብቻ ከከተማ ጥግ አትገዙ
ተፈላጊ ባልሆነ ወይም ገና ባልደገፈ አካባቢ ያለን ርካሽ ንብረት መግዛት ጥሩ እድል አይደለም—ወጥመድ እንጂ።
ጥቂት ብር ለመቆጠብ ብላችሁ በጣም ከከተማ ጥግ ወጥታችሁ መግዛት የፋይናንስ አቅማችሁን በሶስት መንገድ ይጎዳል፦

* የኪራይ ገቢ ማነስ፦ የኪራይ ፍላጎት አነስተኛ በመሆኑ ምክንያት በጣም ዝቅተኛ ወርሃዊ ገቢ ነው የምታገኙት።
* የዋጋ አለመጨመር፦ ከከተማ ውጭ ያሉ ቦታዎች የመሰረተ ልማት እና የዋጋ ዕድገት ለማሳየት ረጅም ጊዜ ይወስድባቸዋል።
* ለመሸጥ መቸገር፦ ነገ ንብረቱን ሸጣችሁ ወደ ሌላ ኢንቨስትመንት መግባት ብትፈልጉ፣ ቤቱን ለመሸጥ ወራት ወይም ዓመታት ሊወስድባችሁ ይችላል።
ሁልጊዜም ቢሆን ጥሩ ቦታ (Location) እና ተደራሽነት ከትልቅ ነገር ግን ርካሽ ቦታ ይበልጣል።

4. ህጋዊ ሰነዶችን በቀጥታ ከምንጩ አረጋግጡ
የህዝብ ቤቶችን፣ ኮንዶሚኒየሞችን ወይም ዳግም የሚሸጡ አፓርትመንቶችን ስትገዙ፣ ህጋዊ ሂደቶችን ማጣራት ምርጫ ሳይሆን ብቸኛው የንብረታችሁ ስጋት መቀነሻ መንገድ ነው።
ውል ከመፈረምዎ ወይም ቅድመ ክፍያ ከመክፈልዎ በፊት፦
* የ5 ዓመት እገዳ፦ ቤቱ በህግ የተቀመጠበትን የ5 ዓመት የመሸጫ እገዳ ማጠናቀቁን በቀጥታ በቶች አስተዳደር ሄዳችሁ አረጋግጡ።

* ዲጂታል ካርታ፦ ቤቱ በህጋዊ መዝገብ ላይ ትክክለኛ እና የተረጋገጠ ዲጂታል ካርታ ያለው መሆኑን ቼክ አድርጉ።
* የመንግስት ኤጀንሲ እውቅና፦ ሁሉም የውል ዝውውሮች በቤቶች ኤጀንሲ የተመዘገቡና ህጋዊ እውቅና ያላቸው መሆናቸውን አረጋግጡ።
መደበኛ ያልሆኑ ውሎችን አምኖ ህጋዊ ማረጋገጫዎችን ችላ ማለት ገዢዎችን ለባለቤትነት ክርክር እና ለሙሉ ገንዘብ ማጣት ያጋልጣል።
5. የውሉን ዝርዝር ነጥቦች መርምሩ (ወይም ጠበቃ ያዙ)
አንዴ ብር ከኪሳችሁ ከወጣ በኋላ፣ የእንደራደር ባይነት አቅማችሁ ወደ ዜሮ ይወርዳል።
የተለመዱ የአልሚዎች ውሎች አብዛኛውን ጊዜ ሻጩን የሚጠቅሙ ናቸው—በውስጣቸውም የግንባታ ጊዜ ማራዘሚያዎችን፣ ያልተጠበቁ የዋጋ ጭማሪዎችን እና የካሬ ሜትር ልዩነቶችን የሚፈቅዱ አንቀጾች ይኖሯቸዋል።
* እያንዳንዱን አንቀፅ እራሳችሁ በጥንቃቄ መርምሩ።
* ከመፈረምዎ በፊት ገለልተኛ የሪል እስቴት ጠበቃ ውሉን እንዲመረምረው ያድርጉ።
* ከሽያጭ ተወካዮች በሚሰጥ የቃል ቃልኪዳን በጭራሽ አትመኑ—በህጋዊ ውሉ ላይ በግልጽ ካልተጻፈ በስተቀር በህግ ፊት ዋጋ የለውም።

በሪል እስቴት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ማለት ህንፃዎችን መግዛት ብቻ አይደለም፤ ሀብትን መጠበቅ እና ስጋትን (Risk) ማስተዳደር እንጂ። ልምድ ያላቸው ኢንቨስተሮች "ይህ ንብረት ምን ያህል ያተርፍልኛል?" ብለው ብቻ አይጠይቁም— "ይህ ግብይት ዋና ሀብቴን እንዴት ያጠናክርልኛል?" ብለውም ይጠይቃሉ።

💡 በሪል እስቴት ግብይቶች ውስጥ ያያችሁት ትልቁ ስጋት ወይም ስህተት ምንድን ነው? አስተያየትችሁን ከታች ኮሜንት ላይ ጻፉልን።
👇 ተግባራዊ የሪል እስቴት ስትራቴጂዎችን፣ የገበያ ትንተናዎችን እና የኢንቨስትመንት ህጎችን ለማግኘት Follow ያድርጉ

የባንክ ብድር መክፈል ባይችሉ ምን ይፈጠራል? በኢትዮጵያ የባንኮች ሕግና አሰራር መሰረት ማወቅ የሚገቡዎት 4 መረጃዎች!ብዙ ሰዎች የጠየቁት ጥያቄ?  ጥያቄ? በባንክ ብድር ቤት ወይም ንብረት ...
03/09/2026

የባንክ ብድር መክፈል ባይችሉ ምን ይፈጠራል? በኢትዮጵያ የባንኮች ሕግና አሰራር መሰረት ማወቅ የሚገቡዎት 4 መረጃዎች!
ብዙ ሰዎች የጠየቁት ጥያቄ? ጥያቄ? በባንክ ብድር ቤት ወይም ንብረት ሲገዙ ብድሩን መክፈል ባልችልስ? የሚለው ነገር መታየት አለበት። በኢትዮጵያ የባንክ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 97/1998) እና በብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች መሰረት ተበዳሪ ክፍያ ሲያቋርጥ ባንኮች የሚከተሏቸውን 4 ህጋዊ ደረጃዎች አሉ።

1️⃣ ተግባር ላይ ያልዋለ ብድር NPL (Non-Performing Loan) እና የቅጣት ወለድ
ክፍያ ካቋረጡበት ቀን ጀምሮ ለ 60 ቀናት (2 ወራት) ያህል ክፍያ ካልፈጸሙ ብድሩ ወደ ያልተከፈለ ብድር (NPL) ይመደባል። ባንኩ መደበኛ ወለዱ ላይ ተጨማሪ የቅጣት ወለድ (Penalty Interest ) ማሰብ ይጀምራል።ባንኩ በመጀመሪያ የስልክ የጽሁፍ እና የውይይት ጥሪ በማድረግ ክፍያውን እንዲፈጽሙ እድል ይሰጣል።

2️⃣ የ 30 ቀን የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ (Final Notice)
ውይይቶች ካልተሳኩ እና ክፍያው አሁንም ካልተፈጸመ ባንኩ በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የ 30 ቀን የጽሁፍ የጥሪ ማስጠንቀቂያ ያስረክባል።በዚህ 30 ቀን ውስጥ እዳዎን ካልዘጋጁ ወይም ከባንኩ ጋር አዲስ የስምምነት ማስተካከያ ካላደረጉህጋዊ እርምጃው ወደ ቀጣዩ ደረጃ ይሸጋገራል።

3️⃣ የሃራጅ/የጨረታ ማስታወቂያ (Foreclosure / Public Auction)
በኢትዮጵያ አዋጅ ቁጥር 97/1998 መሰረት ባንኮች የተያዘውን መያዣ (Collateral) ለመሸጥ ወደ ፍርድ ቤት መሄድ አያስፈልጋቸውም direct የሃራጅ (Auction) ስልጣን አላቸው።
ባንኩ የያዙትን ቤት/ንብረት በጋዜጣ እና በህዝብ ማስታወቂያ ይፋ በማድረግ በጨረታ ይሸጣል።

4️⃣ ንብረቱ ሲሸጥ ሂሳቡ እንዴት ይወራረዳል?
ንብረቱ ከተሸጠ በኋላ ባንኩ የሚፈልገውን ዋና ብድር የተከማቸ ወለድ የቅጣት ክፍያ እና የጨረታ ማስታወቂያ ወጪዎችን ይወስዳል። ትርፍ ገንዘብ ከተረፈ ንብረቱ ከተሸጠበት ዋጋ ላይ የባንኩ እዳ ተቀንሶ የተረፈው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባለቤቱ (ለተበዳሪው) ይመለሳል።
ንብረቱ ካልተሸጠ በቂ ተጫራች ካልቀረበ ባንኩ ንብረቱን በራሱ ግምት ዋጋ የመውሰድ ህጋዊ መብት አለው።

ችግር ሲያጋጥምዎት ከመሸሽ ይልቅ አሁኑኑ ከባንኩ ጋር በመነጋገር መፋታት ተገቢ ነዉ።

የባንክ የረጅም ጊዜ እዳ እና ስጋት ሳይኖርብዎት በየወሩ ለባንክ ከፍተኛ ወለድ ከመክፈል ይልቅ ያለምንም ወለድ በከፈሉት ልክ እጆ ላይ ባለዉ የገንዘብ ዝግጅት ቤት ባለቤት የመሆን እድል ቴምር ፕሮፐርቲስ አቅርቦል።

የወደፊት መኖሪያዎንና ኢንቨስትመንትዎን ያለስጋት ከ ቴምር ፕሮፐርቲስ(Temer Properties) ጋር ያረጋግጡ!

አፓርትመንቶች
📍 ⚡️መገናኛ ⚡️ሳርቤት ⚡️ቡልጋርያ⚡️አዋሬ⚡️አያት
ከ20% ቅድመ ክፋያ ጀምሮ
እስከ የ35% የሚደርስ ቅናሸ አዘጋጅተን እንጠብቆታለን።

🛒የንግድ ሱቆች
📍 ⚡️ሳርቤት ⚡️ፒያሳ ⚡️ቡልጋርያ ⚡️ገላን/ቃሊቲ ከሮቢካ ሆቴል ፊትለፊት
ከ2 ሚሊዮን ብር አጠቃላይ ክፋያ ወይም 900ሺ ብር ቅድመ ክፋያ ጀምሮ አቅርበናል።

ከሀገር ዉጪ ላላችሁ ባላችሁበት ሆናችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ለበለጠ መረጃ
0954258617

Address

Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Beza Homes posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share