24/02/2017
ለኩላሊት ጤንነት የሚጠቅሙ ምግቦች/ Foods For Kidney Health
(በዳንኤል አማረ እና ዳግማዊ ዳንኤል@ኢትዮጤና)
ጤነኛ ኩላሊት ልክ እነደ ልብ በርከት ያሉ ጥቅሞች አሉት፡፡ ኩላሊት በሰውነታችን ውስጥ የሚመረቱ፣ የማይፈለጉ፣ ከመጠን በላይ የበዙ እና መርዛማ የሆኑ ነገሮችን ከደማችን ውስጥ በማጣራት በሽንት መልክ ከሰውነታችን ያስወጋዳል፡፡ በተጨማሪም ኩላሊት በሰውነታችን ውስጥ ያሉትን የኔጌቲቭ ቻርጅ መጠን እና የተለያዩ ፈሳሾችን መጠን ይቆጣጠራል፡፡
✔ ጤናማ ያልሆነ ኩላሊት የሚከተሉት ችግሮች ያስከትላል፦
• ሽንት የመሽናት ችግር
• በአይን አካባቢ እብጠት መፈጠር
• የእግር እና እጅ ማበጥ
• ከብዙ ጊዜ በኋላ የልብ ችግር ያመጣል
• ንጽህናው የተጠበቀና ለጤንነት ጥሩ የሆነ ምግብ መመገብ በሰውነታችን ጤንነት እንዲሁም በትክክል ስራውን እንዲሰራ ያደርጋል፡፡
• በአብዛኛው አንቲ ኦክሲዳንት(Antioxidant) የሆኑ ምግቦች ለምሳሌ፦ እንደ ፍላቮኖይድስ (Flavonoids)፣ ሊኮፔን(Lycopene)፣ ቤታ-ካሮቲን(Beta-carotene) እና ቫይታሚን ሲ(Vitamin C) ንጥረ ነገሮችን የያዙ ምግቦችን የኩላሊት ጤንነትን ይጠብቅልናል፡፡
• አንቲ ኦክሲዳን(Antioxidant) በሰውነታችን ላይ የሚካሄደውን ኦክሲዴሽን(Oxidation) በነፃ ኤሌክትሮን እነዚህ ትርፍ ወይም ነፃ ኤሌክትሮን ዋናው በኩላሊት በሽታ መንስኤ ነው፡፡
✔ለኩላሊት ጤንነት የሚጠቅሙ ምግቦች እነሆ፦
1. ጥቅል ጎመን (Cabbage)
ጥቅል ጎመን የኩላሊት ስራን ያፋጥናል በተጨማሪም ኩላሊትን በመጠገንና ስራውን አቀላጥፎ እንዲሰራ ያደርገዋል፡፡ የኩላሊት ችግር ያለባቸው ሰዎች ጥቅል ጎመንን እንዲመገቡ ይመከራል፡፡
2. ቤሪስ/ፍራፍሬ(Berries)
የማንጋኒዝ፣ ቫይታሚን ሲ፣ ፋይበርና ፎሌት በጣም ጥሩ ምንጭ ነው፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ የቤሪስ ፍራፍሬዎች እንጆሪ፣ ክሬን ቤሪስ፣ ራስፕ ቤሪስ፣ እና ብሉ ቤሪስ ለኩላሊት ጥሩ ናቸው፡፡ ቤሪስ ፀረ ኦክሲዳንት እና ኢንፍላሜሽን ባህሪ አላቸው ስለዚህ የሽንት ፊኛ ተግናሩን በትክክል እንዲወጣ ያግዙታል፡፡ እነዚህ የቤሪስ ፍሬዎችን ወዲያው የተቆረጡ(ትኩስ)፣ የቀዘቀዙ ወይም ደረቅ መጠቀም ሲቻል በጥሬው መመገብ ወይም በመደበኛ የምግብ ዝርዝር ውስጥ በማስገባት መጠቀም ተመራጭ ነው፡፡
3. አሳ (Fish)
የአሳ ስጋ ወይም መረቅ በውስጡ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ(Omega-3 fatty acid) የሚባል ንጥረ ነገር በውስጡ ይዟል፡፡ ይህ ንጥረ ነገር የሰውነት ቆዳችን እንዳይጨማደድ ያገለግላል፡፡ ኩላሊትን ከተለያዩ በሽታዎች ይከላከላል፡፡ በተጨማሪም አሳ ከፍተኛ የሆነ የፕሮቲን ምንጭ ነው ይህ ፕሮቲን ለሰውነታችን አስፈላጊ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ለኩላሊት ጠቃሚ ከሆኑ የአሳ ዝርያዎች መካከል፦ ሳልሞን(Salmon)፣ ሬይንቦ ትሮት(Rainbow trout)፣ማክከረል(Mackere;)፣ ኸሪንግ እና ቱና ናቸው፡፡ እነዚህን አሳዎች ቀቅለን፣ አብስለን፣ ጠብሰን ብንመገብ ይመከራል፡፡
4. የወይራ ዘይት
የወይራ ዘይት ለልብ እና ኩላሊት ጤንነት ከፍተኛ አስተዋጽዎ አለው፡፡ ይህ ዘይት የኦሊክ አሲድ(Antioxidant) ጥሩ ምንጭ ሲሆን ፀረ ኢንፍላማቶሪ አሚኖ አሲድ ነው ኦክሲዴሽንን በመቀነስ የኩላሊት ጤንነት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም በፖሊፌኖል(Poly phenol) እና ፀረ ኦክሲዳንት የበለፀገ ሲሆን ኢንፍላሜሽን (inflammation ) እና ኦክሲዴሽንን በመከላከል ይጠቅሙናል፡፡ የወይራ ዘይትን ከሰላጣ፣ ዳቦ፣ አሳና አትክልቶች ጋር በመቀላቀል መመገብ ጥሩ ውጤት ያስገኛል፡፡
5. ነጭ ሽንኩርት! (Garlic)
ነጭ ሽንኩርት አንቲ ኦክሲዳንት እና የደም መርጋትን በመከላከል ከፍተኛ ከፍተኛ ከሆነ የኩላሊት በሽታ ይታደገናል፡፡ አንድ ወይም ግማሽ ራስ ነጭ ሽንኩርት በየቀኑ በባዶ ሆድ መመገብ ጎጂ የሆነ የኮሌስትሮል መጠንን እና ኢንፍላሜሽንን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም ኩላሊትን በከፍተኛ ብረት(Heavy Metal) የሚከሰትን ጉዳት ይቀናሳል፡፡
6. የኦሊቫ ዘይት! (Olive Oil)
ኦሊቫ ዘይት ጥሩ የኦሊይክ አሲድ ምንጭ ሲሆን ፀረ ኢንፍላማቶሪ ፋቲ አሲድ ነው። በኦሊቭ ዘይት ውስጥ የሚገኝው ፋት ኦክሲዴሽንን ይከላከላል። የኦሊቭ ዘይት በፓሊፌኖል እና ፀረ ኢንፍላሜሽን ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ሲሆን ኢንፍላሜሽን እና ኦክሲዴሽንን ይከላከላል።
7. እንቁላል (ነጩ ክፍል) (White Egg)
የእንቁላል ነጩ ክፍል ፕሮቲን ሲሆን አስፈላጊ የሆኑ አሚኖአሲዶችን ሁሉ በመያዝ ከፍተኛ ጥራት ያለው ፕሮቲን ይለግሰናል። ለኩላሊት በሽተኞች የእንቁላል ነጩ ክፍል ከእንቁላል ቢጫ ክፍል እና ከሥጋ ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ የፎስፈረስ መጠን ስላለው ጠቃሚ ነው።
8. የአበባ ጐመን (Cauliflower)
የአበባ ጐመን በቫይታሚን ሲ ይዞታው ከፍተኛ ሲሆን የፎሌት እና ፋይበር ጥሩ ምንጭ/መገኛ ነው። ኢንዶል (Indole)፣ ግሉኮሲኖሌትስ (Glucosinolates)፣ እና ታዮሲያኔት (Thiocyanates) ውህዶች ክምችት በብዛት ይገኝበታል እነዚህ ውህዶች ሴሎች እና ዲ ኤን ኤ የሚጐድ መርዛማ ነገሮችን ጉበት ለማምከን የሚያደርገውን ጥረት ያግዛል።
9. ቀይ ወይን (Red Grapes)
ቀይ ወይን በውስጡ ቀይ ቀለም እንዲይዝ ያደረጉትን ፍላቮኖይድ (Flavonoid) በብዛት ይዟል። ፍላቮኖይድ ኦክሲዴሽንን በመከላከል እና የደም መርጋትን በመቀነስ የልብ በሽታን ይከላከላል። ረስቬራትሮል (Resveratrol) የተባለው በወይን ውስጥ የሚገኝ ፍላቮኖይድ ናይትሪክ ኦክሳይድ እንዲመረት ያነሳሳል ይህም የደም ቧንቧ ጡንቻ ሴሎችን ዘና እንዲሉ በማድረግ የደም ፍሰትን ይጨምራል።
10. እንጆሪ (Strawberry)
እንጆሪ በሁለት ዓይነት ፌኖሎች የበለፀገ ነው፦ አንቶሲያኒንስ እና ኢላጂታኒንስ በተባሉ። አንቶሲያኒንስ እንጆሪ ቀይ ቀለም እንዲኖረው የሚያደርገው ነው በተጨማሪም ጠንካራ ፀረ ኦክሲዳንት ሲሆን የሰውነታችን ሴሎች ቅርፅን እና በኦክሲዴሽን የሚደርስ ግዳትን ይከላከላል። እንጆሪ እጅግ በጣም ጥሩ የቫይታሚን ሲ፣ ማንጋኒዝ እና ፋይበር መገኛ ሲሆን የልብና የኩላሊትን ጤንነት በመጠበቅ ይታወቃሉ።
መልካም ጤንነት!!
ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ
https://www.facebook.com/EthioTena