Nassir Hussen Hamedu

Call Directions Contact the business

Nassir Hussen Hamedu ኢትዮጵያ አፋር ሠመራ ���

ቱርክ በኔቲኒያሁ ላይ የእስር ትእዛዝ ስታወጣ ኔታኒያሁ ደግሞ ቱርክ ቀጠናውን ስታበጣብጥ ዝም ብለን አናይምና እንዋጋለን እያለ ነው።የሁለቱ ሀገራት መፍካከር ፉከራ ብቻ ሆኖ ይቀራል ወይንስ ይ...
21/08/2026

ቱርክ በኔቲኒያሁ ላይ የእስር ትእዛዝ ስታወጣ ኔታኒያሁ ደግሞ ቱርክ ቀጠናውን ስታበጣብጥ ዝም ብለን አናይምና እንዋጋለን እያለ ነው።

የሁለቱ ሀገራት መፍካከር ፉከራ ብቻ ሆኖ ይቀራል ወይንስ ይባቀሳሉ የሚለውን ጊዜ ቢነግረንም አሁን ላይ ግን በእስራኤል እና ኢራን መካከል እናይ የነበረውን የቃላት ጦርነት ወደ ቱርክና እስራኤል ተሸጋግሯል።

እናም ሁለቱ ሀገራት " ይዋጣልና!" እያሉ ነው። የመፋለሚያ ሜዳቸው ደግሞ ሶሪያ !

ሁለቱ የቀጠናው ሀያላን ሀገራት በርግጥ ቶሎ ወደ ጦርነት ይገባሉ ተብሎ አይታሰብም። ውድመቱ ሁለቱንም የሚያደቅ ስለሚሆን። ይሁን እንጅ ጦርነቶች ሁሌም በስሌት ብቻ አይከሰትም። እንደውም ብዙ ጊዜ በተሳሳቱ ስሌቶች ( Miscalculations) ነው የሚከሰቱት።

እናም ሁለቱ ዝሆኖች ይራገጣሉ ወይንስ ተፏክረው ይለያያሉ ?

ሁኔታዎች ግን ወደ ቀጥታ መላተም እየገፏቸው ይገኛሉ!

“መንግሥት ካሸነፈ በኋላ የተሸነፈውን ኃይል በፕሪቶሪያው ስምምነት አስቀምጦ ተደራድሮ፣ በችግር ውስጥ የነበሩ ኃይሎችን ቀልቦ እና ብዙ ድጋፍ ሰጥቶ ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል” ጠቅላ...
11/08/2026

“መንግሥት ካሸነፈ በኋላ የተሸነፈውን ኃይል በፕሪቶሪያው ስምምነት አስቀምጦ ተደራድሮ፣ በችግር ውስጥ የነበሩ ኃይሎችን ቀልቦ እና ብዙ ድጋፍ ሰጥቶ ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ የማንም ጅል፣ ጅላጅልና ጅላንፎ ጥምረት መጫወቻ አትሆንም!ጅሉ ሸኔ፡- ለራሳቸው ሳይነቁና ራሳቸውን ከደህነት ነጻ ሳያወጡና ከጫካ ህይወት ነፃ አውጪ ነን ባዮች ሲሆኑ እነዚህ ጅሎች እ...
10/08/2026

ኢትዮጵያ የማንም ጅል፣ ጅላጅልና ጅላንፎ ጥምረት መጫወቻ አትሆንም!

ጅሉ ሸኔ፡- ለራሳቸው ሳይነቁና ራሳቸውን ከደህነት ነጻ ሳያወጡና ከጫካ ህይወት ነፃ አውጪ ነን ባዮች ሲሆኑ እነዚህ ጅሎች እውነትን የሚቃረኑ እና ሁልጊዜ ስለ ችግርና ባርነት ብቻ ለህዝብ የሚተነትኑና ህዝብን የሚሰቃዩ ናቸው። እነዚህ ሁልጊዜ በመፍትሄ ላይ ሳይሆን በ"አሉታዊ ኃይል" ላይ ስለሚያተኩሩ እና ገንቢ ውይይት ስለማያደርጉ ኢትዮጵያን የመምራት ዕድል አያገኙም።

ጅላጅሉ ፋኖ፡- ጅላጅል ማለት ሌላውን ጅል እንደ አዋቂ ቆጥሮ የሚከተል እና ለጅል ሃሳብ ዋጋ የሚከፍል ነው። እነዚህ አካላት መጓዛቸውን እንጂ መድረሻቸውን፣ መሰብሰባቸውን እንጂ አጀንዳቸውን፣ እንዲሁም ማመጻቸውን እንጂ ግባቸውን አያውቁም። እነዚህን ሰዎች እንደ "ተሳቢ" የሚጎተቱት ናቸው።

ጅላንፎዎቹ ሕወሓቶች፡- ጅላንፎዎች ዋናውን ጅል እንኳን አያውቁትም፤ ነገር ግን በሰፈር ጅላጅል የሚነዱ ናቸው። አንድ ነገር በሰፈር ሲሰሙ ለማሰብ ጊዜ ሳይወስዱ ወዲያውኑ ውሳኔ ላይ የሚደርሱና የሚንቀሳቀሱ ናቸው። አሁን ላይ ጅላንፎው ሕወሓት ሌላውን ጅል (ሻዕቢቢያንና ግብፅን በመከተል) እነሱ ወደፈለጉበት አቅጣጫ እየተነዳ ነው’

አገራዊ ምክክሩ «ለአክሱም ሙስሊሞች መብት መከበር ትኩረት ይስጥ!» ሲሉ ጄነራል ሳሞራ የኑስ ጠየቁ‼===============   ''የአክሱም ሙስሊሞች በተወለዱበት ከተማ መስጂድ መሰራት እና ...
10/08/2026

አገራዊ ምክክሩ «ለአክሱም ሙስሊሞች መብት መከበር ትኩረት ይስጥ!» ሲሉ ጄነራል ሳሞራ የኑስ ጠየቁ‼
===============

''የአክሱም ሙስሊሞች በተወለዱበት ከተማ መስጂድ መሰራት እና መቀበር አይችሉም'' ሲሉ የቀድሞው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሳሞራ የኑስ ተናገሩ።

ሰሞኑን በአገራዊ የምክክር ኮሚሽን መድረክ ላይ በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ጄነራል ሳሞራ፣ በዚሁ ማእቀፍ በአጀንዳነት እንዲያዙላቸው ካቀረቧቸው መሰረታዊ አጀንዳዎች መካከል የአክሱም ሙስሊሞች የኃይማኖት ነጻነት ጉዳይ ዋነኛው እንደሆነ ተነግሯል። ባለፉት ጊዜያት ኢትዮጵያ ውስጥ የሀይማኖት እኩልነትና አካታችነት ሲከበር እንዳልነበር በአጽንኦት የጠቀሱት የቀድሞው ኢታማዦር ሹም፣ ለዚሁ መከራከሪያቸው እንደ ዋነኛ ግብአት አድርገው በዚሁ መድረክ ያቀረቡት ደግሞ የአክሱም ሙስሊሞች ጉዳይ ነው ተብሏል። "የአክሱም ሙስሊሞች በተወለዱበት አክሱም ከተማ መስጂድ መስራትና መስጂድ ውስጥ መቀበር አይችሉም" ያሉት ሳሞራ "ይህ መብት እንዲከበር ምክክር ኮሚሽኑ እገዛ ያድርግ" ሲሉ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል ተብሏል።

ጄነራሉ፣ "የኃይማኖት እኩልነትና አካታችነት አላከበረም" ብለው ዛሬ የሚወቅሱትን የቀድሞ ስርአት በጠቅላይ ኤታማዦር ሹምነት እንዳገለገሉት የሚታወቅ ቢሆንም በዚህ ቁልፍ የስልጣን እርከን ላይ ለ17 አመታት ያህል ሲቆዩ ግን ይህን መብት እንዲከበር ያደረጉት ጥረት ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም።

"ወደ ጫካ የገባነው ምክክር ስላልነበረ ነዉ።" ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ኢትዮጵያ እየመከረች ነው።
10/08/2026

"ወደ ጫካ የገባነው ምክክር ስላልነበረ ነዉ።"

ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው።

ትልቅ የኢኮኖሚ ዜና፦ ኢትዮጵያ ከማዕድን ኤክስፖርት ከ5.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ!ኢትዮጵያ ከማዕድን ምርቶች ወጪ ንግድ ከ5.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን...
10/08/2026

ትልቅ የኢኮኖሚ ዜና፦ ኢትዮጵያ ከማዕድን ኤክስፖርት ከ5.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ!

ኢትዮጵያ ከማዕድን ምርቶች ወጪ ንግድ ከ5.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን Ethiopian Business Review ዘግቧል። በአዲሱ በጀት ዓመትም ገቢውን ወደ 6.7 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ ግብ መቀመጡን ዘገባው ያመለክታል።

ይህ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትልቅ ዜና ነው። በተለይ ወርቅና ሌሎች የማዕድን ምርቶች የውጭ ምንዛሬ ምንጭ እየሆኑ መምጣታቸው፣ የማዕድን ዘርፉ በኢትዮጵያ የኤክስፖርት ኢኮኖሚ ውስጥ ያለው ሚና እየጨመረ መሆኑን ያሳያል። የUNDP የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ግምገማም የአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት በግንቦት 2026 ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ መድረሱን፣ ወርቅና ቡና ኤክስፖርት ለዚህ ዋነኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጠቁሟል።

በአጠቃላይም የኢትዮጵያ ኤክስፖርት በቅርብ ጊዜ ከፍተኛ እድገት እያሳየ ሲሆን፣ በ2025/26 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ 8 ወራት ብቻ አጠቃላይ የኤክስፖርት ገቢ 6.76 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተዘግቧል።

ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የማዕድን ሀብት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ በግልጽ አስተዳደርና እሴት በሚጨምር ምርት ከተጠቀመችበት፣ ዘርፉ ከአገሪቱ ትልልቅ የውጭ ምንዛሬ ምንጮች አንዱ የመሆን አቅም አለው።

በቀጠናው በጀግናው (FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት)የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፊት መቆም የሚችል አንድም ኃይል የለም‼️(መፈራገጥ ትርፉ መላላጥ ብቻ ነው)
10/08/2026

በቀጠናው በጀግናው (FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት)የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፊት መቆም የሚችል አንድም ኃይል የለም‼️

(መፈራገጥ ትርፉ መላላጥ ብቻ ነው)

🇮🇷 ጋዜጠኛ፦ «ጦርነቱን ማን አሸነፈ?»🇮🇷 አራግቺ፦ «እነሱ ጦርነቱን ከጀመሩ በኋላ በ48 ሰዓት ውስጥ ኢራንን ሙሉ በሙሉ እንቆጣጠራለን ብለው አስበው ነበር።»🇮🇷 ጋዜጠኛ፦ «ታዲያ?»🇮🇷 አ...
09/08/2026

🇮🇷 ጋዜጠኛ፦ «ጦርነቱን ማን አሸነፈ?»

🇮🇷 አራግቺ፦ «እነሱ ጦርነቱን ከጀመሩ በኋላ በ48 ሰዓት ውስጥ ኢራንን ሙሉ በሙሉ እንቆጣጠራለን ብለው አስበው ነበር።»

🇮🇷 ጋዜጠኛ፦ «ታዲያ?»

🇮🇷 አራግቺ፦ «አሁን ግን 184ኛው ቀን ላይ ደርሰናል። እነሱ የሆርሙዝ ባሕር መተላለፊያን አጥተዋል።በመላው መካከለኛው ምሥራቅ የነበሯቸውን ወታደራዊ መሠረቶችም አጥተዋል።

ለትራምፕም ምስጋና ይገባውና ከሆርሙዝ 100 ቢሊዮን ዶላር እናገኛለን። እንግዲህ ማን እንዳሸነፈ አንተ ንገረኝ።» 🔥🇮🇷

Address

Afar Semera
Logya

Telephone

+251923654525

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nassir Hussen Hamedu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Nassir Hussen Hamedu:

Shortcuts

Share

Category