Lijalem Atinkut ልጅ እያሱ ዘ መራዊ

Lijalem Atinkut  ልጅ እያሱ ዘ መራዊ ወዳጀ ለመኖር ብላ እንጅ ለመብላት አትኑር

ማንችስተር ሲቲ ከ ብሬንትፎርድ፣ ሊቨርፑል ከ ቼልሲ*************በ36ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ሲቲ ብሬንትፎርድን ያስተናግዳል። ከ...
09/05/2026

ማንችስተር ሲቲ ከ ብሬንትፎርድ፣ ሊቨርፑል ከ ቼልሲ
*************

በ36ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ሲቲ ብሬንትፎርድን ያስተናግዳል። ከኤቨርተን ጋር ነጥብ መጋራቱን ተከትሎ የሊጉን ዋንጫ የማንሳት ዕድሉ ሙሉ በሙሉ ከእጁ የወጣው ማንችስተር ሲቲ፣ አሁንም ያለውን ጥቂት ዕድል ለመጠቀም እና በአርሰናል ላይ ጫና ለማሳደር ወደ ሜዳ ይገባል።

ሆኖም ዘንድሮ ጠንካራ የውድድር ጊዜ ያሳለፈው ብሬንትፎርድ፣ የአውሮፓ መድረክ ተሳትፎን ለማግኘት እየታገለ በመሆኑ ጨዋታው ለሲቲ እጅግ ፈታኝ እንደሚሆን ይጠበቃል። በተለይ ክሪስታል ፓላስ እና አስቶን ቪላ በዩሮፓ ሊግ እና በኮንፈረንስ ሊግ ለፍጻሜ መድረሳቸውን ተከትሎ፣ በቀጣይ ዓመት በአውሮፓ መድረክ የሚሳተፉ የእንግሊዝ ክለቦች ቁጥር ሊጨምር ስለሚችል በ51 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ብሬንትፎርድ ይህንን አጋጣሚ ለመጠቀም ይፋለማል።

በኢትሃድ ስታዲየም በሚደረገው ጨዋታ ሮድሪ ለዛሬው ፍልሚያ ሊደርስ እንደሚችል አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግሯል። ጋርዲዮላ ትላንት በሰጠት መግለጫ "በዛሬው ጨዋታ ከተሸነፍን የዋንጫው ጉዞ በይፋ ያበቃል" ሲል የጨዋታውን ወሳኝነት ገልቷል። ሲቲ ካሸነፈ ከአርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት የሚያጠብ ይሆናል፡፡

ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ ሊቨርፑል እና ቼልሲ የሚገናኙበት ጨዋታ ይጠበቃል። በፕሪሚየር ሊጉ ያለፉትን ስድስት ተከታታይ ጨዋታዎች የተሸነፈው ቼልሲ፣ ዛሬም በአንፊልድ ሌላ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል። ሊጉ ሊጠናቀቅ ሦስት ጨዋታዎች ብቻ እየቀሩት እስካሁን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን ያላረጋገጠው ሊቨርፑል፣ ከዛሬው ጨዋታ ሦስት ነጥብ ካገኘ መሳተፉን በይፋ የሚያረጋግጥ ይሆናል። በአንፊልድ በሚደረገው ጨዋታ ሞሃመድ ሳላህ እና አሊሰን ቤከር አሁንም በጉዳት ከስብስቡ ውጭ ናቸው። በቼልሲ በኩል ሌቪ ኮልዊል እና ሬስ ጄምስ ለጨዋታው ሊደርሱ ይችላሉ ተብሏል።

በሻምፒዮንስ ሊግ መሳተፉን ቀድሞ ያረጋገጠመው ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሜዳው ወጭ ከሰንደርላንድ 11 ሰዓት ላይ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ ብራይተን ከ ዎልቭስ እና ፉልሀም ከ ቦርንማውዝ ሌሎች ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

Shor Like & Follow እያደረጋችሁ

06/05/2026
 #ስፖርት በእንግሊዝ የእግር ኳስ መድረክ እጅግ ተቀናቃኝ በሆኑት ሁለቱ ታላላቅ ክለቦች መካከል በኦልድ ትራፎርድ የተካሄደው የዘንድሮው ፍልሚያ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 3-2 በሆነ ...
03/05/2026

#ስፖርት

በእንግሊዝ የእግር ኳስ መድረክ እጅግ ተቀናቃኝ በሆኑት ሁለቱ ታላላቅ ክለቦች መካከል በኦልድ ትራፎርድ የተካሄደው የዘንድሮው ፍልሚያ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 3-2 በሆነ አስገራሚ ውጤት ባሸነፈበት ልብ አንጠልጣይ ትዕይንት ተጠናቋል። ይህ ታሪካዊ ድል ማንቸስተር ዩናይትድን ከሁለት ዓመታት መራቅ በኋላ ዳግም ወደ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መድረክ የመለሰ ሲሆን፣ የድሉ ዋነኛ ጀግና የሆነው ወጣቱ ኮቢ ማይኖም ከሶስት ቀናት በፊት የፈረመውን አዲስ የአምስት ዓመት ኮንትራት ወሳኟን የማሸነፊያ ግብ በማስቆጠር አክብሯል።

ቀያዮቹ ሰይጣኖች ጨዋታውን በከፍተኛ የበላይነት በመጀመር፣ በማቲዩስ ኩኛ እና ቤንጃሚን ሴስኮ ቀድመው የተገኙ ግቦች ታግዘው የመጀመሪያውን አጋማሽ 2-0 መምራት ችለው ነበር። ሆኖም ከእረፍት መልስ የጨዋታው መልክ ሙሉ ለሙሉ ተቀየረ። ሊቨርፑሎች በከፍተኛ መነቃቃት ወደ ሜዳ በመመለስ፣ የተገኙትን የተከላካይ ክፍል ስህተቶች በሚገባ ተጠቅመው በዶሚኒክ ሶቦስላይ እና ኮዲ ጋክፖ አማካኝነት ተከታታይ ግቦችን በማስቆጠር ጨዋታውን ወደ አቻ ውጤት መለሱት።

ይሁን እንጂ በከፍተኛ ፉክክር ወደ ፍጻሜው ሲቃረብ፣ ሊቨርፑሎች ከግራ መስመር በሉክ ሾው የተሻገረውን ኳስ በአግባቡ ማስወገድ ተስኗቸው ኳሷ በሳጥኑ ጠርዝ ላይ ለነበረው ማይኖ ተመቻችታ ደረሰችው። በቀድሞው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ስር በሊጉ የቋሚነት እድል አግኝቶ የማያውቀው ይህ ድንቅ ታዳጊም፣ ያገኛትን ኳስ ሳይቆጣጠር በአንዴ መሬት ለመሬት በመምታት የሊቨርፑልን መረብ በማናጋት የኦልድ ትራፎርድን ስታዲየም በደስታ አናወጠው።

ከጨዋታው አስቀድሞ ታላቁ የቀድሞ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በድንገተኛ ህመም ምክንያት ለጥንቃቄ ሲባል በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል በተወሰዱበት በዚህ ምሽት የተገኘው ድል፣ ለዩናይትድ ደጋፊዎች ልዩ ትርጉም አለው። ከሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ማረጋገጥ ባሻገር፣ ከ2015-16 የውድድር ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሊቨርፑል ላይ የደርብ ድል (በሜዳም ከሜዳ ውጭም ማሸነፍ) በማስመዝገብ የኩራት ባለቤት አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል ተሸናፊው ሊቨርፑል የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን ለማረጋገጥ አሁንም ቀሪ አራት ነጥቦች ያስፈልጉታል።

ይህ እጅግ ጣፋጭ ውጤት፣ የጊዜያዊ አሰልጣኙን ማይክል ካሪክን ክለቡን በቋሚነት የመምራት ተስፋ በከፍተኛ ደረጃ አልሞታል። ካሪክ እስካሁን ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ ሊቨርፑልን፣ ማንቸስተር ሲቲን፣ አርሰናልን፣ ቶተንሀምን እና ቼልሲን በማሸነፍ የእንግሊዝን ታላላቅ ክለቦች በሙሉ ጠራርጎ ማሸነፍ ችሏል። የጨዋታው ድባብም እጅግ ሞቅ ያለ ነበር፤ የቡድኑ አንበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ቡድኑ የውጭ ውርወራ ባገኘበት አንደኛው አጋጣሚ ደጋፊውን በስሜት እንዲጮህ ሲያነቃቃ፣ ከስታዲየሙ የተመለሰለት አስገራሚ እና ነጎድጓዳማ ምላሽ የድሉን ጀብድ እና የተጫዋቾቹን የትግል መንፈስ በሚገባ የሚያሳይ ነበር።

🔵 ማንቸስተር ሲቲ ወደ መሪነቱ ለመመለስ ተቃርቧል! 🏆የዘንድሮው የፕሪሚየር ሊግ የሻምፒዮንነት ፉክክር መልክ እየቀየረ ይገኛል። ማንቸስተር ሲቲ ዛሬ ረቡዕ በርንሌይን የሚያሸንፍ ከሆነ፣ ከነሐ...
22/04/2026

🔵 ማንቸስተር ሲቲ ወደ መሪነቱ ለመመለስ ተቃርቧል! 🏆

የዘንድሮው የፕሪሚየር ሊግ የሻምፒዮንነት ፉክክር መልክ እየቀየረ ይገኛል። ማንቸስተር ሲቲ ዛሬ ረቡዕ በርንሌይን የሚያሸንፍ ከሆነ፣ ከነሐሴ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሊጉ መሪ መሆን የሚያስችለውን ወርቃማ እድል አግኝቷል።

በሌላ በኩል በርንሌይ ዛሬ ሽንፈት ካስተናገደ ከወዲሁ በይፋ ከሊጉ መሰናበቱን ያረጋግጣል።

🔥 የሁኔታዎች መለዋወጥ፦

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ሲቲ አርሰናልን 2 ለ 1 ማሸነፉን ተከትሎ፣ የነጥብ ልዩነቱ ወደ 3 ዝቅ ብሏል። ዛሬ ሲቲ በርንሌይን ከአንድ ጎል በላይ ልዩነት ካሸነፈ፣ እኩል 70 ነጥብ ይዞ በጎል ልዩነት ብልጫ አርሰናልን በመብለጥ የሊጉን መሪነት ይረከባል።

📉 በደረጃው ግርጌ ያለው ትንቅንቅ፦

ለበርንሌይ ይህ ጨዋታ የሞት ሽረት ነው። ሽንፈት የሚያስተናግዱ ከሆነ ከወዲሁ ከሊጉ መውረዳቸው ይረጋገጣል።

📋 የቡድን ዜናዎች፦

🔹 ማንቸስተር ሲቲ፦ ሩበን ዲያስ እና ጆስኮ ግቫርዲዮል አሁንም ከጉዳት አልተመለሱም። ፔፕ ጋርዲዮላ ለኤፍኤ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ ሲል በአሰላለፉ ላይ መጠነኛ ለውጥ ሊያደርግ ይችላል።

🔹 በርንሌይ፦ እንደ ጆሽ ኩለን እና ኮኖር ሮበርትስ ያሉ ቁልፍ ተጫዋቾች በጉዳት አይሰለፉም።

⏰ የጨዋታ ሰዓት፦ ምሽት 4:00

ግምታችሁን አስቀምጡ! 👇 ሲቲ መሪነቱን ይረከባል ወይስ በርንሌይ ተአምር ይሰራ ይሆን?

https://www.facebook.com/profile.php?id=61588553025410
follow Like & Sher ያድርጉ

22/04/2026

ሚስት ለመፈለግ በ Ticktock ብወጣ
ሀምሳ ሽህ ደብዳቤ ቤቴ ድረስ መጣ

ሁሉንም ከፍቸ ባነበው ባነበው
የኔን ውሰድ ብለው ወንዶች የላኩት ነው

የዘንድሮ ነገር ከባድ ነው ሚስጥሩ
ሴቶች እባካችሁ ወንዱን አታማሩ

ወንዱን አታማሩ

ወንዱን አታማሩእእ
ወንዱን አታማሩሩሩእ

 #ጋምቤላን በከብቶቻቸዉ ያጥለቀለቁት ማህበረሰቦች እነማን ናቸዉ?ሰሞኑን ጋምቤላ ከተማን ያጥለቀለቀዉ የከብት መንጋ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ በርካታ እንስሳት እና ባለቤቶቻቸዉን ጓዛቸዉን ሳይቀር ...
10/04/2026

#ጋምቤላን በከብቶቻቸዉ ያጥለቀለቁት ማህበረሰቦች እነማን ናቸዉ?

ሰሞኑን ጋምቤላ ከተማን ያጥለቀለቀዉ የከብት መንጋ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ በርካታ እንስሳት እና ባለቤቶቻቸዉን ጓዛቸዉን ሳይቀር ጭነዉ ሲጓዙ ታይተዋል፡፡ ይህ የፈላታዎች አርብቶ አደር ማህበረሰብ ጉዞ ነዉ፡፡ የእነዚህ ማህበረሰቦች ሕይወትና ጉዞ በዓለማችን ላይ ካሉ እጅግ አስገራሚና ረጅም ከሆኑ የሰው ልጅ ስደቶች አንዱ ነው።

እነዚህ ሕዝቦች ከምዕራብ አፍሪካ (በተለይም ከሴኔጋል፣ ማሊ፣ ጊኒና ናይጄሪያ) ተነስተው አህጉሪቱን አቋርጠው እስከ ኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ድረስ የሚያደርጉት ጉዞ ከታሪክ፣ ከሃይማኖትና ከኑሮ ዘይቤ ጋር የተቆራኘ ነው።
ስለ እነዚህ ተጓዦች አስገራሚ ሕይወት ጥቂት ነጥቦች እነሆ፦

👉"የማያቋርጥ ጉዞ"
ፈላታዎች በዋናነት ከብት አርቢዎች ናቸው። ጉዟቸው በዘፈቀደ የሚደረግ ሳይሆን "የግጦሽ መሬት ፍለጋ" እና "መንፈሳዊ ጉዞን" (ሐጅ) መሰረት ያደረገ ነው። ከምዕራብ አፍሪካ ተነስተው ቻድንና ሴንትራል አፍሪካን አቋርጠው ሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር ለመድረስ አንዳንዴ ዓመታት ሊፈጅባቸው ይችላል። በዚህ ረጅም ጉዞ ውስጥ ልጆች ይወለዳሉ፣ አዛውንቶች ያልፋሉ፤ ሕይወት በመንገድ ላይ ይቀጥላል።

👉ከከብቶቻቸው ጋር ያላቸው ጥብቅ ቁርኝት
ለፈላታዎች ከብት ማለት የሀብት መለኪያ ብቻ ሳይሆን የክብርና የሕይወት መሠረት ነው።
ከብቶቻቸው የረጅም ርቀት ጉዞን የሚቋቋሙ፣ ትላልቅ ቀንድ ያላቸውና ጠንካራ ናቸው።
ገበሬውና ከብቶቹ በፉጨትና በልዩ ድምፅ ይግባባሉ።
አንድ ፈላታ ከብቶቹን እንደ ቤተሰቡ ነው የሚንከባከባቸው፤ ለብቻቸው ለይቶ በስም ይጠራቸዋል።

👉የኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር - "የመጨረሻው መድረሻ"
ብዙዎቹ ፈላታዎች በሱዳን በኩል አድርገው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር (በተለይ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ አካባቢ) ይደርሳሉ።
ወደ ኢትዮጵያ ድንበር የሚጠጉት ፈላታዎች በእርሻ ስራ (በተለይም ጥጥና ሰሊጥ በመቅጠፍ) እና በእንሰሳት ንግድ የታወቁ ናቸው።
ቀደም ባሉ ጊዜያት ብዙዎቹ ወደ መካ ለመሄድ በእግር ጉዞ ሲጀምሩ ኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ላይ ለረጅም ጊዜ ያርፉ ነበር። አንዳንዶቹም እዚያው እየተቀላቀሉ ቀርተዋል።

👉ልዩ ባሕላቸውና አለባበሳቸው
ፈላታዎች በየትኛውም ቦታ ቢሆኑ ማንነታቸውን አያጡም፦
አለባበስ፦ ወንዶቹ ሰፊ ኮፍያ እና ረጅም ልብስ ይለብሳሉ። ሴቶቻቸው ደግሞ በቀለማት ያሸበረቁ ልብሶች፣ ትላልቅ የወርቅ ወይም የናስ ጉትቻዎችና በፊታቸው ላይ የሚደረጉ ንቅሳቶች ይታወቃሉ።

👉ጽናት፦ በበረሃ፣ በጫካና በወንዞች ውስጥ የሚያደርጉት ጉዞ እጅግ አደገኛ ቢሆንም፣ ተፈጥሮን የማንበብና የመላመድ ብቃታቸው የሚደነቅ ነው።

👉"ፉላኒ" በኢትዮጵያ
ምንም እንኳን መነሻቸው ምዕራብ አፍሪካ ቢሆንም፣ ዛሬ ላይ በምዕራብ ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ያሉ ፈላታዎች ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ተቀላቅለው፣ ቋንቋ ተምረውና ዜግነት አግኝተው የሚኖሩ ጥቂት አይደሉም። የንግድ ስራን በማቀላጠፍና ዘመናዊ የእንሰሳት እርባታን በማስተዋወቅ ረገድም ሚና አላቸው።

ይህ በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ የመሄድ ባህል፣ ፈላታዎችን በአፍሪካ ውስጥ "የድንበር የለሽ ሕዝቦች" ተምሳሌት ያደርጋቸዋል።

Please Follow ፣ Like & Sher

29/03/2026

የእውነት ኢትዮጵያ ውስጥ ሁና አረብ ሀገር እንዳለች መስላ ብዙ ጊዜ እንዲህ የምትለኝ ልጅ ነበረች እናም አንድ ቀን እንዲህ አለችኝ እናቴ ታማ ሆስፒታል እንደገባች ሰማሁ ወንድሜንም በ online ነበር የማገኘው አሁን online ላይ ከጠፋ ሰነባበተ ስልክ እንዳልደውል ስልኬን ከአሰሪወቸ ጋ ነውና እባክህ በዚህ ቁጥር ደውለህ ያሉበትን ሁኔታ አጣርተህ ንገረኝ አለችና የወንድሜ ስልክ ነው ብላ የሆነ ቁጥር ሰጠችኝ ከዛ እኔም ታዲያ አሁን አንች በምን online እየተጠቀምሽ ነው እኔን የምታወሪኝ ስላት ከአሰሪወቸ እየተደበቅሁ በኮምፒውተር ነው የምጽፍልህ አለችኝ እኔም እውነት መስሎኝ በዚያ በሰጠችኝ ቁጥር ስደውል የሆነ ወጣት ልጅ አነሳውና ያለውን ሁኔታ አወራኝና በመጨረሻ የመድሀኒት መግዣ ብር የለኝም አሁንም እሷ ትልካለች ብየ ከሰው ተበድሬ ነበር ግን አለቀብኝ እና ፈጠን አድርጋ እንድትልክልኝ ንገርልኝ አለኝና ስልኩን ዘጋው እኔም ወዲያውኑ ልጁ ያለኝን አንድ ሳላስቀር በ online ሁሉንም ነገርኳት ከዚያ ልጅት ምን ብትለኝ ጥሩ ነው ዛሬ አሰሪወቸ ሌላ ቦታ በስራ ጉዳይ ወጥተው ነውና ሲመለሱ ብር ልላክልህና አንተ ላክልኝ አለችኝ እኔም በራሱ በወንድምሽ አካውንት ለምን ማትልኪለት ስላት ወንድሜ አካውንት የለውም አለችኝና እኔም እሽ ብየ የምትፈልገውን የባንክ አካውንት ሰጠኋትና ጠበቅኋት ሳትልክ ሰነበተችና በሌላው ቀን Hi አለችኝ እኔም ሰላም ነሽ ምነው ጠፋሽ አልኳት እሷም አሰሪወቸ ከሄዱበት ስለተለሱ ኮምፒውተር ለመጠቀም ፈርቸ ነው አሁንም ተደብቄ ነው የምጽፍልህ አለችኝ እንደለመደችው እኔም እንደራሴ መስሎኝ በይ እሽ አልኳት እሷም ብሩን ልልክል ነው ስትለኝ እሽ አልኳት ከዚያ ከ2+3 ስዓት የሚሆን ቆያይታ ብሩ በኤጀንቶች ተመንዝሮ ወዳንተ እንዲላክ ለኤጀንቶች አስረክቢያለሁ እናም ለኤጄንቶች ኮሚሽን ያስፈልጋልና እኔ የዚያን ሁሉ አስቤ ነው የላክሁልህና ስልክህን ሰጥቻለሁ ኤጀንቶች ደውለው በሚሰጡህ አካውን 8,000 ብር ላክላቸው አለችኝና ቻው ቻው አሰሪወቸ መጡብኝ ብላ ከ online ወጣች ከዚያ በሌላው ቀን የሆነ ስልክ ተደወለልኝና ሳነሳው የሆነ የድርጅት ስም ጠርቶ የድርጅቱ ኤጀንት ነኝ አለኝና እከሌ የላከችልህ ብር አለ እናም በምልክልህ አካውንት ለድርጅታችን ኮሚሽን 8,000 ብር አስገባና ብሩ ይላክልህ አለኝ እኔም ወንድሜ ብር የለኝ አልኩት እንግዲያውስ ብሩ ወደመጣበት ሀገር ይመለሳል አለኝ እኔም ይመለሳ አልኩትና ስልኬን ዘጋሁት ከዚያ ልጅት በሌላኛው ቀን እንደተለመደው online ገባችና Hii አለችኝ እኔም ሰላም ነሽ እንዴት ነሽ አልኳት ቀጠለችና ለምንድነው መጀመሪያ ወዳንተ የማልከውን ብር ካስላከኝ በኋላ ለኤጀንቶች አልከፍልም ብለህ ብሩን ወደኔ ያስመለስከው አለችኝ እኔም የዋዛ አይደለሁም መለስኩና ቆይ ለምን ከሚመነዝሩት ብር ላይ ይሄን 8,000 ብር ቀንሰው ቀሪውን አይልኩልኝም ነበር አልኳት እሷም እንደዛማ አይቻልም የኤጀንቶች ህግ ነው አለችኝ እኔም ብር የሚባል የለኝም በጭራሽ አልልክም ስላት ይገርማችኋል ሰደበችኝና ጭራሽ ብሎክ አደረገችኝ እስኪ እናንተ ብትሆኑ 8,000 ብሩን ትልኩ ነበር ? ሀሳባችሁን በኮመንት አካፍሉኝ ።

 ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ›› (ሉቃ.፩፥፲፱)የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ ‹‹እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ›› ማለት ነው...
28/03/2026


‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ›› (ሉቃ.፩፥፲፱)

የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ ‹‹እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ›› ማለት ነው፤ ‹‹ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢይተረጐም ምሥጢር ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር፤ ገብርኤል ሆይ ተመራምሮ ለማይደረስበት ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፤ ነገር ግን አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ይመስላል›› እንዲል፡፡ (መልክዐ ቅዱስ ገብርኤል)

ቅዱስ ገብርኤል የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት እና ሰው መሆን ለመናገር ተልኮ የምሥራች ዜናን ያበሠረ፤ በዲያቢሎስ የተንኮል ወጥመድ ገብተው ለተሰናከሉት ፈጥኖ ለርዳታ የሚደርስ፣ በጨለማ እና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩት ሁሉ የብርሃን ፋና ያበራ፣ ሰብአ ሰገልን የመራ መልአክ ነው፡፡ ከቀድሞ ጀምሮ ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ተልከው መንፈስ ቅዱስ እንዳናገራቸው ዓለምን ስለማዳን ከጽዮን የሚወጣ ከያዕቆብ በደልን የሚያርቅ ጌታ ‹‹ይወርዳል ይወለዳል›› በማለት በየወገናቸው እና በየዘመናቸው የተናገሩትን የነቢያትን ትንቢት ያስፈጸመና የምሥራችን ቃል የተናገር፣ የጨለማ አበጋዝ በሆነ በሰይጣን ተንኮል ከእፉኝት መርዝ የከፋ በሰው ልቦና ውስጥ አድሮ የነበረውን የኀዘን ስሜት ያጠፋ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል እና ክብሩ

ቅዱስ ሉቃስ እንደጻፈው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሁል ጊዜም ለደስታና ለምሥራች የሚላክ መልአክ ነው፤ በተለይም ስለ ልደተ ክርስቶስ ለድንግል ማርያም ለመጀመሪያ ጊዜ የምስጋና እና የክብር ሰላምታ ያበሠረ በመሆኑ ‹‹አብሳሬ ትስብእት (መልአከ ብሥራት) መጋቤ ሐዲስ›› ተብሎ ይጠራል፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ መላእክት ከተፈጠሩ በኋላ አምላካቸውን ለማወቅ ‹‹መኑ ፈጠረነ›› እያሉ ሲባዝኑ ሳጥናኤል ‹‹እኔ ፈጠርኳችሁ›› ሲል ቅዱስ ገብርኤል ግን የፈጠረንን አምላክ እስክናውቅ ድረስ በያለንበት እንቁም እንጽና፤ ንቁም በበህላዌነ እስከ ንረክቦ አምላክነ›› በማለት መላእክትን ያረጋጋ መልአክ ነው፡፡ (አክሲማሮስ. ገጽ.፴፭) በዚህም አባቶቻችን እንደሚሉት መልአኩን የመጀመሪያው የተዋሕዶ ሰባኪ ነው፡፡ ምክንያቱም ከፍጥረታት አስቀድሞ አምላኩን ዐውቆ ስብከት የጀመረ መልአክ ነውና፡፡ በዚህም ምክንያት ጌታ ‹‹ወበእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም፤ድንግል ማርያምን ያበስር ዘንድ የተገባው ሆነ›› እንዲል፤ ነገረ ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበሥር አድሎታል፤ ከዚህ በኋላም ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ ዘወትር በምንጸልያቸው ጸሎቶች ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡ ይኸውም በዘወትር ጸሎቶች በአቡነ ዘበሰማያት፣ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል፣ በውዳሴ ማርያም፣ በይዌድስዋ መላእክት እና በመሳሰሉት ጸሎቶች ዘወትር ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ካህናት አባቶች እንደሚሉት ስእለት ሰሚ እንዲሁም ፈጥኖ ደራሽ መልአክ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በክርስቲያኖችም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ መልአክ ነው፡፡ ስለዚህም ፈጥኖ ደራሹ መልአክ፣ ስእለት ሰሚው መልአክ ይባላል፡፡ በሀገራችንም ክብረ በዓሉ በቁልቢ ገብርኤል እና በተለያዩ ቦታዎች እጅግ በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት ይከበራል፡፡

የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከሌሎች መላእክት ሁሉ በይበልጥ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን እንደ ምትወደው በድርሳነ ገብርኤል ላይ ተጽፏል፤ ‹‹ርእዩኬ አኃዊነ ዘከመ ታፈቅሮ እግዝእትነ ማርያም ለቅዱስ ገብርኤል እምኲሎሙ መላእክት እስመ አብሠራ ልደተ ወልድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ወውእቱ ከመ ያፈቅራ ወይረድኣ በጊዜ ምንዳቤሃ ለነኒ ይርድአነ በጊዜ ምንዳቤነ፣ ወንድሞቻችን ሆይ፥ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከመላእክት ሁሉ ይልቅ ቅዱስ ገብርኤልን በይበልጥ እንደምትወደው ተመልከቱ፤ የልጅዋን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ መወለድ ያበሠራት እርሱ ነውና›› እንዲል፡፡ (ድርሳነ ገብርኤል ዘኅዳር ምዕራፍ ፪፥ ቁጥር ፲፫)

ቅዱስ ገብርኤል ብርሃናዊ መልአክ ነው፤ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ በራእዩ እንዲህ በማለት ተናግሯል፤ ‹‹ከዚህ በኋላ ታላቅ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች፡፡›› (ራእ.፲፰፥፩)

ነቢዩ ዳዊት ‹‹መላእክቱን የእሳት ነበልባል የሚያደርግ›› እንዳለው ቅዱስ ገብርኤል ነበልባላዊ መልአክ ነው፡፡ (መዝ.፻፫፥፬)

ቅዱስ ገብርኤል ኃያል መልአክ ነው፤ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ‹‹ብርቱ መልአክ ደመና ተጎናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዐምዶች ነበሩ፤ የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ፤ ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፤ እንደሚያገሳም አንበሳ በታላቅ ድምጽ ጮኸ›› በማለት መስክሯል፡፡ (ራእ.፲፥፩)

ቅዱስ ገብርኤል የመላእክት አለቃ ነው፤ በራማ በሠፈሩት ዐሥሩ የነገድ ሠራዊት ላይ የአርባብ አለቃ ነው፡፡ ነቢዩ ሄኖክም ‹‹በሠራዊት ሁሉ ላይ የተሾመ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው›› ይላል፡፡ በዚህም ምክንያት የራማው መልአክ ተብሎ ይጠራል፡፡ (ሄኖክ.፲፥፲፬)

ቅዱስ ገብርኤል ፈጣን መልአክ ነው፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚሉት በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥነ ስቅለት ጊዜ በመስቀል ላይ የደረሰበትን መከራ አይቶ አላስችለው ቢል ሰይፍ ወርውሯል፤ ‹‹ዓለምም የሚያልፈው ቅዱስ ገብርኤል የወረወረው ሰይፍ ሲያርፍ ነው›› ይላሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ መልኩም ሰይፍ እንደወረወረ ከዚህ በታች በተጻፈው መልኩ እንገነዘባለን ይኸውም፡-

ሰላም ለሰኰናከ ወለመከየድከ ክልኤ

ታሕተ ዐውደ መስቀል ዘቆማ በዕለተ ድልቅልቅ መውዋዔ

ሰይፈ ቁጥዓ ገብርኤል ዘመላኅከ ቅድመ ጉባኤ

አንስትሰ ሶበ ሰምዓ ቃለ ዚኣከ በቋዔ

ኀበ ሐዋርያት ሖራ ይንግራ ትንሣኤ

ትርጉም፡- ገብርኤል ሆይ፥ በዚያ ድብቅልቅና ሽብር በሆነበት ዕለት ከጌታ እግረ መስቀል ሥር ለቆሙት ተረከዞችህና ጫማዎችህ ሰላም እላለሁ፤ ገብርኤል ሆይ የጌታን ትዕግሥት የአይሁድን ግፍ ተመልክተህ በታላቅ ዐደባባይ ላይ ሰይፈ ቁጣህን አምዘገዘግኸው ቅዱሳት አንስት ግን ክርስቶስ ተነሥቷል ስላልካቸው የትንሣኤውን ምሥራች ይነግሩ ዘንድ ወደ ሐዋርያት ሄዱ›› እንዲል፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ገብርኤል ከዓለም በፊት አምላኩን ያወቀ ዓለም ልታልፍ ስትልም የወረወረው ሰይፍ እንደሚያርፍ ሊቃውንቱ ያስረዳሉ፡፡

በሀገራችን በተለምዶም ‹‹ሚካኤል እንደአየህ ገብርኤል እንዳያይህ›› የሚባል አባባል አለ፤ ይኸውም የመልአኩ ተራዳኢነት እንዳለ ሁኖ ተነግሮ ለማይሰማ አካል ግን መልአኩ ፈጣን እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም የቅዱስ ገብርኤልን ቁጣ የምንሰማ እና የምናይ ሲሆን ለምሳሌም ካህኑ ዘካርያስ የመልአኩን ቃል ባለመስማቱ (ባለመቀበሉ) ዲዳ ሁኗል፡፡በተጨማሪም በኢ-አማንያንም ዘንድ ሳይቀር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ይፈራል፡፡ (ሉቃ.፩፥፲፩)

ቅዱስ ገብርኤል እና ተራዳኢነቱ

ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ሰማዕታትን ገድላቸውን እንዲፈጽሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደኋላ እንዳይመለሱ ተጋድሏቸውን እንዲጨርሱ ይረዳቸዋል፡፡ (ዳን.፫፥፳፭) ክርስቶስ በስደት ሲሰደድም ሲመለስም እንዲናገር የተላከ መልአክ ነው፡፡ (ማቴ.፪፥፲፱፣ሉቃ.፪፥፰)

ቅዱስ ገብርኤል የእግዚአብሔር ባለሟል ነው፤ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነኝ›› እንዲል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ማለቱ ለእግዚአብሔር የተወሰነ ፊት ኖሮት ማለትም እንደ ንጉሥ ወታደር በእግዚአብሔር ፊት ተገትሮ የሚቆም መሆኑን ለመግለጽ አይደለም፡፡ ምንጊዜም ከእግዚአብሔር የማይለይ መሆኑን እና አማላጅነቱን ለመግለጽ ነው እንጅ፡፡ (ሉቃ.፩፥፲፱)

ቅዱስ ገብርኤል ምእመናንን የሚጠብቅ ጠባቂ መልአክ ነው፤ ስለዚህም ምሥክር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንመልከት፤ ‹‹በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል››እንዲል (መዝ.፺፩፥፲፩)፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል››(መዝ.፴፬፥፩)፤ ‹‹በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ፡፡››(ዘጸ.፳፫፥፳)

ቅዱስ ገብርኤል እና ክብረ በዓሉ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን መላእክትን ወርኃዊ እና ዓመታዊ በዓላቸውን በጸሎት እና በምስጋና ታከብራለች፡፡ በተለይም ታኅሣሥ ፲፱ ቀን የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በዓል የሚከበርበት ምክንያት ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አግብርተ እግዚአብሔር አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን (ሠለስቱ ደቂቅን) ከእቶነ እሳት ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ በግእዝ የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስም ‹‹ትማልም አሲረነ ሠለስተ እደወ ወደይነ ውስተ እቶነ እሳት ዮምሰ እሬኢ አርባዕተ እደወ እንዘ ያንሶሰዉ ማዕከለ እሳት ፍቱሐኒሆሙ ወገጹ ለራብዓይ ወልደ እግዚአብሔር ይመስል››፤ ትናንት ሦስት ሰዎች አስረን ከእሳቱ እቶን ጥለን ነበር፤ ዛሬ ግን ዐራት ሆነው ከእሥራታቸው ተፈትተው በእሳቱ ውስጥ ሲመላለሱ አያለሁ፤ ዐራተኛውም የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል፤ በማለት ይገልጸዋ፡፡ (ወዲያውም ከእቶኑ ሂዶ‹‹ አንትሙ ሲድራቅ ወሚሳቅ ወአብድናጎ አግብርተ እግዚአብሔር ንዑ ፃዑ ዝየ፤ ኑ ውጡ›› አላቸው ብር ብር እያሉ ከእሳቱ ውስጥ ወጥተዋል፤ በልብሳቸው ላይም ጥላሸት እንኳን አልተገኘም፤ ናቡከደነጾርም ይህን አይቶ አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን አለ፤ ንጉሡም አዋጁን በአዋጅ መልሶ ለሕጻናቱ በሹመት ላይ ሹመት በክብር ላይ ክብር ጨምሮላቸዋል)፡፡

የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት እና ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይኑር፤ አሜን፡፡

Indirizzo

LosAngeles California
Verona

Sito Web

Notifiche

Lasciando la tua email puoi essere il primo a sapere quando Lijalem Atinkut ልጅ እያሱ ዘ መራዊ pubblica notizie e promozioni. Il tuo indirizzo email non verrà utilizzato per nessun altro scopo e potrai annullare l'iscrizione in qualsiasi momento.

Contatta L'azienda

Invia un messaggio a Lijalem Atinkut ልጅ እያሱ ዘ መራዊ:

Scelte rapide

Condividi

Digitare