16/11/2025
ቸርች እንዴት ነበር?
(How was Church?)
"...በስራው የላቀ አምላክ ..."
መዝሙር 19:1-4 NASV
[1] ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያውጃሉ። [2] ቀን ለሌላው ቀን ይናገራል፤ ሌሊትም ለሌሊት ዕውቀትን ይገልጣል፤ [3] ንግግር የለም፤ ቃል የለም፤ ድምፃቸው በጆሮ የሚሰማ አይደለም። [4] ያም ሆኖ ድምፃቸው በምድር ሁሉ፣ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ይወጣል። እርሱ በሰማያት ለፀሓይ ድንኳን ተክሏል፤
✍️ እግዚአብሔር አምላካችን ልሁቅ የሆነ አምላክ ሲሆን፤ ልህቀት የሚመነጨው ከእርሱ ዘንድ ነው። የእግዚአብሔር የእጆቹ ስራዎች እና ፍጥረታት የእርሱን ልህቀት ያሳያሉ። ሌላኛው ደግሞ በመዋጀት ስራው /Redemption/ ውስጥ ያደረገው ትልቅ ማሳያ ነው።
የእግዚአብሔር ትልቁ የልህቀት ስራው የታየው ሰውን ባዳነበት የማዳን መንገድ ውስጥ ነው፤ ፍጹም የሆነው እቅዱ ፍጹም ፍቅሩን ተሸክሞ ታይቷል።
ኤፌሶን 1:7-8 NASV
[7] በርሱም እንደ እግዚአብሔር ጸጋ ባለጠግነት መጠን፣ በደሙ በተደረገ ቤዛነት፣ የኀጢአት ይቅርታ አገኘን፤ [8] ጸጋውንም በጥበብና በማስተዋል ሁሉ አበዛልን።
የእግዚአብሔር የማዳኑ ስራ የሚያሳየው የእግዚአብሔርን የሥነ ምግባር ልህቀት ማለትም ቅድስናውን እና ፍትህን፣ የእግዚአብሔርን መንፈሳዊ ልህቀት ማለትም ፍቅሩን ምህረቱን እና ታማኝነቱን እንዲሁም የእግዚአብሔርን አፈጣጠር ማለትም ኃጢአትን እና ሞትን ወደ ድል እና አዲስ ሕይወት መቀየሩን ያሳያል።
የእግዚአብሔር ሁሉን ነገር መቆጣጠር ልህቅነቱን የሚያሳይ ነው። በዚህም ምክንያት ነው ፍጥረትን ሳይሆን ፍጥረትን እንዲፈጠር ያደረገውን እግዚአብሔር አድናቂ መሆን ያለብን።
💫 Even when life seems chaotic, God's wisdom and purpose are flawlessly at work. And He waves excellence through every event.
የእግዚአብሔርን ልህቀት መለኪያ ያደረጉ ነገሮች ደግሞ የእርሱ ቅድስና (የሞራል ልዕልና) ሲሆን፤ እግዚአብሔር ከየትኛውም አይነት እንከን እና ጉድለት የጸዳ ነው። የእርሱ የፍትህ መንገድ ፍጹም ነው።
የእርሱ ጥበብ (ፍጹም እይታ) ደግሞ ፍለጋ የለውም፤ ወይንም መጨረሻ የሌለው ነው። በዚህም ምክንያት “እግዚአብሔር ጋር ስትደርስ ገና እየጀመርክ ነው፤ ስትነካው ገና አልያዝከውም…”
ሮሜ 11:33 NASV
[33] የእግዚአብሔር የጥበቡና የዕውቀቱ ባለጠግነት እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ አይመረመርም፤ ለመንገዱም ፈለግ የለውም!
በመጨረሻም እግዚአብሔር በእያንዳንዱ በሰራቸው ስራዎቹ ውስጥ ልህቀት እንደሚታይ ሁሉ የእኛን የልጆቹን ሕይወት በእያንዳንዱ አቅጣጫ በልህቀት ሊሞላ እና ከእርሱ ከልህቅነቱ ከወጡ ሀሳቦች፣ አደራረጎች እና ሀብቶች ወደ ማይነጥፍ ብልጽግና ሊከተን ይፈልጋል።
ሬቨ. ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
ቀን እሁድ 07/03/2018
⛪️ የክብር ሕይወት ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
መልካም የመነሳትና የማብራት ምሽት!