04/10/2023
የልጆች አዕምሮ ፈጣን እድገት እንዲኖረው የሚያደርጉ 7 ምግቦች!
➖〰️➖🧠〰️➖〰️🧠🧠➖〰️➖🧠〰️➖〰️
የልጆች አዕምሮ ፈጣን እድገት እንዲኖረው የሚያደርጉ ሰባት ምግቦች የሚከተሉት ናቸው:-
1️⃣ እርጎ 🥤🥛
አእምሮ ላይ መልዕክት በተገቢው እንዲላክና እንዲቀበል ይረዳል፤ ቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ አለው፤ ይህ ደግሞ የአእምሮ ህብረ ህዋሶችና መልእክት አስተላላፊዎች በተገቢው እንዲያድጉ ይጠቅማል።
2️⃣ አትክልቶች 🥬🥕🥒🥗
አትክልቶች አንቲ ኦክሲደንትነት አላቸው፤ ይህ ደግሞ የአዕምሮ ህዋሶች ጤናማ እንዲሆኑ ይረዳል። ለምሳሌ እንደ ስኳር ድንች፣ ዱባ፣ ካሮት ያሉትን መስጠት እንደባሮ ሽንኩርት፣ እስፒናች፣ ቆስጣ ያሉት ደግሞ በፎሌት የበለፀጉ ስለሆኑ ልጆችን ከመርሳት በሽታ ይከላከላሉ።
3️⃣ ብሮኮሊ 🥦🥦
ካንሰር ተከላካይነት ባህሪ አለው በተጨማሪም የነርቭ ስርዐት በተገቢው የተያያዘ እንዲሆን ያግዛል።
4️⃣ አቦካዶ 🥑🥑
አስፈላጊ ቅባት አለው፤ ይህም በቂ ደም ወደ ጭንቅላት እንዲዘዋወር ይረዳል። ኦሊክ አሲድ በመያዙ ምክንያት ማይሊን የተባለውን የአዕምሮ ክፍል ከመጥፎ ነገር ይከላከለዋል(ማይሊን በሰዐት በ200 ማይል ፍጥነት መልዕክት እንዲተላለፍ ያደርጋል)። በቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ የበለፀገ መሆኑ ልጆች በግፊት የመያዝ እድላቸውን ይቀንሳል።
5️⃣ አሳ 🐠🐟
አሳዎች በኦሜጋ 3 የበለፀጉ በመሆናቸው የልጆች አእምሮ ፈጣን እድገት እንዲኖረው ይረዳሉ።
6️⃣ እንቁላል 🥚🥚
የተለያዩ ንጥረ ነገሮች አሉት፤ ለምሳሌ ኦሜጋ 3፣ ዚንክ፣ ኮሊን(አሴታይል ኮሊን) እንዲመረት የሚረዳ ሲሆን የማስታወስ ችሎታን ለማዳበር ያግዛል።
7️⃣ የተፈጨ አጃ 🌾🌾
በተለይ ለቁርስ ብንመግባቸው ጥሩ የማስታወስ ችሎታ እንዲኖራቸው ይረዳል፤ በተጨማሪም በቫይታሚን ኢ፣ ዚንክ፣ ቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ የበለፀገ ነው። ከፍተኛ ፉይበርነት ስላለው ኃይልን እንዲያገኙም ያደርጋል።
መልካም ጤንነት!!
ምንጭ፦ fb Chef Ermias Tadese(ሄልዝላይን)
መስከረም 23/2016 ዓ.ም